Logo
YenetaTube
በምርጫ አሸንፈው ምክር ቤት ከገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ የመስራት ዓላማ ያለው "ኮከስ" ለመመስረት ማቀዱን ኢዜማ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በ2019 ዓ.ም. ሥራ በሚጀምረው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን "ኮከስ" በመመስረት የመሥራት እቅድ እንዳለው አስታውቋል።

ፓርቲው እንደ አብን ካሉ ምክር ቤት ለመግባት የሚያስችላቸውን ድምጽ ካገኙ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በሚያስማሙ የመታገያ አጀንዳዎች ላይ ለመስራት እንዳቀደ ገልጿል።

የኢዜማ የስራ አስፈጻሚ አባል አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን እንደገለጹት፤ ፓርላማ በገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚመሰረተው ኮከስ አላማ በምክር ቤቱ የጋራ አጀንዳዎችን በማቅረብ ተጽዕኖ መፍጠር ነው።

ጥምረቱ ለሕዝብ የሚጠቅሙ ጉዳዮች በገዢው ፓርቲ ተቀባይነት እንዲያገኙ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ለዚህ ተግባራዊነትም ፓርቲው ከአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ምክክር ጀምሯል ተብሏል።)አርክቴክት ዮሐንስ እንዳብራሩት፤ ጥምረቱ በዋናነት በሕዝብ ጥቅም ላይ ያተኮሩ ጉዳዮችን ለመደገፍ የታለመ ነው።

ፓርቲው የሀገርን ሉዓላዊነት ማስጠበቅና የብሔርተኝነት እሳቤን መታገል እንደ ዋና ግቡ ማስቀመጡን እና ህዝብን በሚጠቅሙ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ግን ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል።

ይህ የትብብር ስልት በምክር ቤቱ ውስጥ ለሚደረጉ ውይይቶች ሚዛን ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ አርክቴክቱ ገልጸዋል
#አሐዱ

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.