“ የኢትዮጵያን ቅርጫ የሚመኙ አሞሮች አንድ ኪሎ ስጋ መውሰድ አይችሉም ! "
ጠ/ ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
----------------------------------------
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ ታሪካዊ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ ስትገነባ የማይታዩ፣ ነገር ግን ስትጨቃጨቅ ብቻ ከየአቅጣጫው የሚያንዣብቡ “አሞሮች” በሀገር ጥቅምና ሉዓላዊነት ላይ የሚያደርሱትን ጣልቃ ገብነት በጥብቅ አስጠነቀቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠንባሮ አባቶች ተረት በመጥቀስ፣ ከብት ሲገዛ የማይሳተፉ፣ ነገር ግን ሲታረድ በየአካባቢው የሚያንዣብቡ አሞሮች፣ የኢትዮጵያ ውስጣዊ አለመግባባትን ተጠቅመው የሀገርን ጥቅም ለመሸርሸር እንደሚሞክሩ አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፣ ኢትዮጵያ ከጉንደት እስከ ባድመ ባሳለፈችው ታሪክ ሁሉ፣ ውስጣዊ መቃቃር በተፈጠረ ቁጥር ጊዜ ጠብቀው ጣልቃ የሚገቡ ኃይሎች መኖራቸውን አስታውሰዋል።
በተለይም ለሺህ ዓመታት የኢትዮጵያ ባለቤትነት የነበረውን ቀይ ባህር ያጣንበት አጋጣሚ፣ ከውጭ ጥቃት ይልቅ በውስጥ ስንፍናና መከፋፈል የመጣ መሆኑን በማውሳት፣ አሁን ላይ ያሉ ፕሮፖጋንዳዎችም የዚሁ እኩይ ተግባር መገለጫ መሆናቸውን ገልጸዋል።
“የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ነገር ሊያውቅ ይገባል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በውስጣችን የሚነሱ ክርክሮች በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መፈታት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
“ከብቱን መርጠን የምንገዛ እኛ ነን፣ የቅርጫውን ባለቤት የምንወስን እኛ ነን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ከፈቃዳችን ውጪ ማንም አካል የኢትዮጵያን ጥቅም በጉልበት መውሰድ እንደማይችል በግልጽ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በቀላሉ በማይበጠስ ገመድ የተሰናሰለች አገር መሆኗን በማስታወስ፣ የውጭ ኃይሎች በፕሮፖጋንዳ ሊያደናግሯት እንደሚችሉ መገመታቸው ከንቱ ምኞት መሆኑን ተናግረዋል። አያይዘውም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪኩን በትክክለኛው መንገድ በመረዳት፣ በጋራ ጥቅምና በአንድነት ላይ እንዲያተኩር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
# Fm 97.1

3 months ago