አከራዮች ላይ ከተማ አስተዳደሩ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ አለ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያን 11.5 በመቶ ማድረጉን ተከትሎ፣ ሕግን በመጣስ በህገ-ወጥ መንገድ የቤት ኪራይ ጭማሪ በሚጠይቁ አከራዮች ላይ ከባድ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
በተለይም ተከራዮችን “ቤቱን ለራሴ ወይም ለዘመዴ እፈልገዋለሁ” በሚል ሐሰተኛ ምክንያት በማስለቀቅ፣ በምትኩ ከፍተኛ የኪራይ ዋጋ በመጫን፣ የ11.5 በመቶውን ጭማሪም ሕጋዊ አስመስለው የመጫን ተግባራት በስፋት እየተስተዋሉ ነው።
በተጨማሪም፣ አከራዮች በውል ሰነድ ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ11.5 በመቶ ጣሪያ በመጥቀስ በሕጋዊ መንገድ እየተስማሙ፣ በተግባር ግን በአፍ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ በመደራደር ተከራዩን ለከፍተኛ የገንዘብ ጫና የሚዳርጉበት የ”ድርብ ውል” አሰራር የተለመደ እየሆነ መምጣቱን የተሰጡ ጥቆማዎች ያመለክታሉ። ይህ ድርጊት በግልጽ ሕግ ተጠያቂ የሚያደርግ ሕገ-ወጥ ተግባር መሆኑን ቢሮው አስገንዝቧል።
በዚህ ረገድ ተከራዮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል። በተለይም በአፍ የተጠየቀው ከፍተኛ የክፍያ ዋጋ በውል ሰነድ ላይ ካልተቀመጠ፣ ተከራዮች ክፍያቸውን ሁልጊዜ በባንክ በኩል ብቻ እንዲፈጽሙ በማድረግ ሕገ-ወጥነቱን በማስረጃነት እንዲይዙ መክሯል።
ቢሮው አክሎም፣ አከራዮች መተሳሰብና ሰብአዊነትን እንዲያስቀድሙ ጥሪ በማቅረብ፣ ሕግ ተላልፈው በሚገኙት ላይ ከባድ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ በጥብቅ አስጠንቅቋል። ማህበረሰቡም ይህንን ሕገ-ወጥ ተግባር በጋራ ለመከላከል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
Seledadotio

3 months ago