የትራምፕ ወቀሳና ዛቻ በኔቶ ጉባኤ
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ ጉባኤ ዛሬ በአንካራ ቱርክ ተጀምሯል። በጉባኤ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደቀደሙት ጊዜያት ሁሉ የኔቶ አባል ሀገራትን ሲወቅሱ፣ በስፔይን ላይ ሲዝቱ፤ ግሪንላንድንም ሲያስፈራሩ ተሰምተዋል።
ጉባኤው ከመጀመሩ አስቀድሞ ትራምፕ ከኔቶ ዋና ጸሀፊ ማርክ ሩተ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት በኔቶ ደስተኛ አለመሆናቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በግሪንላንድ ጉዳይ እንዲሁም ቁጥር አንድ የሽብር ደጋፊ ባሏት በኢራን ጉዳይ ሊረዱን ባለመፈለጋቸው በኔቶ ደስተኛ አይደለንም ብለዋል። ስፔይንን አስፈሪ የኔቶ አባል ሲሉ የተቹት ትራምፕ ከአሁን በኋላ ከስፔን ጋር ምንም ዓይነት የንግድ ግንኙነት አይኖረንምም ብለዋል። ትራምፕ ዛሬ ከስፔን ጋር አገራቸው የነበራትን የንግድ ግንኙነት እንደምታቋረጥ ዝተዋል።
ትራምፕ አሁንም ቢሆን የኔቶ አባል የሆነችውን የዴንማርክን ግዛት ግሪንላንድ የመጠቅለል ፍላጎታቸውን ከመናገር አልተቆጠቡም። ግሪንላንድ ለኛ በጣም አስፈላጊ ስትሆን ለዴንማርክ ግን አስፈላጊ አይደለችም ያሉት ትራምፕ አሁንም እንደሚፈልጓት አጽንኦት ሰጥተዋል።
«እኛ የምንፈልጋት ለዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጥበቃ ለማድረግ ነው» በማለት ትራምፕ «ግሪንላንድን መያዝ እኛን ይረዳናል ለዴንማርክ ግን የሚፈይደው አይኖርም» ሲሉም ሞግተዋል።
የኔቶ ዋና ፀሀፊ ማርክ ሩተ እየጨመረ በመጣው የዩናይትድ ስቴትስ ግሪንላንድን የመጠቅለል ፍላጎት ላይ ለመነጋገር ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አሳስበዋል። ይሁንና የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜተ ፍሬድሪክሰን በበኩላቸው ግሪንላንድ «ለሽያጭ እንደማትቀርብ» ኮፕንሀገን ግልጽ አድርጋለች ብለዋል።
DW Amharic

3 months ago