Logo
FastMereja
5 የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

​ቀን፦ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.

​#fastmereja I በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ቁጥጥርና ክትትል ህገ-ወጥ አሰራር ሲተገብሩ የተገኙ አምስት የነዳጅ ማደያዎች ላይ እንደ ጥፋት ደረጃቸው የዕገዳ እና የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ ተወሰደባቸው።

​በተደረገው የክትትል ስምሪት መሠረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘው ኖክ ነዳጅ ማደያ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አልፋ ነዳጅ ማደያ ህገ-ወጥ አሰራር በማከናወናቸው ከነዳጅ አቅርቦት እንዲታገዱ ተደርጓል። በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ተባረክ ነዳጅ ማደያ ከተፈጸመው ጥሰት አሳሳቢነት አንጻር ከነዳጅ አቅርቦት ለአንድ ወር ሙሉ እንዲታገድ ውሳኔ ተላልፎበታል።

​በሌላ በኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ የሚገኘው የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ የሚገኘው ኦላ ነዳጅ ማደያ ከዚህ ድርጊታቸው ተቆጥበው ወደ ትክክለኛ አሰራር እንዲመለሱ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማው አስተዳደር በነዳጅ ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን እና መደበኛ አሰራርን የሚያስተጓጉሉ አሰራሮችን ለመግታት የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.