የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተከናወነው የመቅጃ ልኬት ምርመራ፣ የመቅጃ ማሽኖች ልኬት ችግር በታየባቸው ማደያዎች ላይ ተገቢው የህግ እርምጃ ተወስዷል ሲል የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሳወቀ ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ወ/ሮ ሃላፊ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፣ በሁለት ነዳጅ ማደያዎች የመቅጃ ማሽን የልኬት ችግር በመገኘቱ ከነዳጅ አቅርቦት ለሁለት ወራት እንዲታገዱ ተደርጓል። እርምጃ የተወሰደባቸው የነዳጅ ማደያዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘው ኖክ ነዳጅ ማደያ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አልፋ ነዳጅ ማደያ ናቸው ብለዋል።
እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ተባረክ ነዳጅ ማደያ ከነዳጅ አቅርቦት ለአንድ ወር እንዲታገድ ተደርጓል የተባለ ሲሆን፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ የሚገኘው የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ የሚገኘው ኦላ ነዳጅ ማደያ የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አክለውም፣ ቢሮው በከተማው ውስጥ ልኬትን በማዛባት ፍትሃዊ የንግድ ውድድርን የሚያደናቅፉ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የጀመረውን የክትትልና የሕግ ማስከበር እርምጃ ይበልጥ በማጠናከር እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም

3 months ago