Logo
Getu Temesgen
እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ14ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 818 እጩ መምህራንን አስመረቀ።
#ethiopia | በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዊ ብሄ/አስ ዋና አሥተዳዳሪ እና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ እንዳለው ፥ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የገጠመውን ስብራት ለመጠገን ከተመራቂዎች ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።

ቃልኪዳናችሁ እውን እንዲሆን እስከአሁን ያገኛችሁትን እውቀት ትውልዱ ላይ ብርሃን እንዲያበራ ከራሳችሁ ጋር የተስማማችሁ ሁኑ ሲሉም አሳስበዋል ።

ተመራቂ እጩ መምህራን ልጆች የሚፈልጉትን እውቀት ለማስጨበጥ የተዘጋጃችሁ ብቁ ትውልዶች ናችሁ ነው ያሉት።

ትውልዱ ላይ በተሰጣችሁ አደራና በገባችሁት ቃል ኪዳን ላይ አተኩራችሁ ስሩ ብለዋል።

"ሀገር ካለች ሁሉም አለ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በምክንያት የምታምኑ እና ከሁሉም ከግለሰባዊ ጉዳይ ሀገራችሁን አስቀድሙ "ነው ያሉት።

ወደ ፊት ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በዕውቀታቸው እንዲያገለግሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን ጌታቸው አድማስ፥ተመራቂዎች ከብዙ አመታት ትጋትና ጥረት በኋላ ለምረቃት በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከተመሠረተ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በዲፕሎማ መርሐ ግብር ከ30ሺህ በላይ ምሩቃንን ለሀገር አበርክቷል።

በ2018ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለ14 ዙር በመደበኛው፣በኤክስቴንሽንና በክረምት መርሃ ግብር በዲግሪና በዲፕሎማ ያሠለጠናቸውን 818 እጩ መምህራንን ነው ያስመረቀው።

ከነዚህም ውስጥ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሰለጠኑ ለመጀመሪያ ጊዜ 322 መምህራንን በዲግሪ በማስመረቅ አዲስ የስኬት ምዕራፍ ላይ መድረሱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ፣ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ጎን ለግን ራሱን ለማስተዳደር በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ልማቶች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

ተመራቂዎች የእናንተ አስተምህሮ የነገዋን ኢትዮጲያ የሚቀርፅ ነው ብለዋል። ስለሆነም በመምህርነት ሙያችሁ የትውልድንና የሀገርን አደራ እንድትወጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መምህር ማለት ህዝብን የመገንባት ተልዕኮ ነው ያሉት ዲኑ የዛሬ የዲግሪና የዲፕሎማ ሰርትፍኬት የጉዞ መጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ሀላፊነት መጀመሪያ ነው ብለዋል።

ወላጆች የኢኮኖሚ ችግር ተቋቁማችሁ ለልጆቻችሁ ትምህርት ቅድሚያ ሰጣችሁ አስተምራችኋልና ክብር ይገባችኋል ።

በትምህርት የመገንባት ሂደት ላይ የተሳተፉትን መምህራን ፣የኮሌጁ አመራሮች እና ሰራተኞች ዲኑ አመስግነዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ከኮሌጁ ባገኙት ዕውቀት እና ክህሎት ለአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተግበራ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ እጩ መምህራን የዋንጫና የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.