Logo
Getu Temesgen
ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ 2026 ሩት ይርጋለም ወደ ሮቤ ከተማ አቀናች
#ethiopia | ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ 2026 እና የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሩት ይርጋለም የባህል፣ የጥበብና የታሪክ ጉብኝቷን በመቀጠል ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ተገኝታለች።

ሩት ይርጋለም ከዚህ ቀደም በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ያደረገችውን ጉብኝት ካጠናቀቀች በኋላ ወደ ባሌ ዞን በማቅናት የአካባቢውን ባህላዊ እሴቶች፣ የጥበብ ቅርሶች እና ታሪካዊ መስህቦች ለመጎብኘት ፕሮግራም ጀምራለች።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ጉብኝቱ አምባሳደሯ ስለ ኢትዮጵያ ባህል፣ ጥበብና ታሪክ ተጨባጭ ግንዛቤ እንድታገኝ እንዲሁም የሀገሪቱን ባህላዊ እሴቶች በዓለም አቀፍ መድረኮች በተሻለ ሁኔታ እንድታስተዋውቅ ያግዛል።

አምባሳደር ሩት ይርጋለም በዋቆ ጉቱ አየር ማረፊያ ስትደርስ በሀዳ ሲንቄዎች፣ በባሌ ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አመራሮች እና በዞኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.