(ዘ-ሐበሻ ዜናኦ) "የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ይብቃ፣ ጦርነት ይቁም፣ እናቶች ልጆቻቸውን መቅበራቸውን ያቁሙ" ሲሉ ዶከተር አብርሀም በላይ አሳሰቡ፡፡ አቶ አብርሀም በላይ ዛሬ በኤክስ ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት ‹‹የትግራይ ነዋሪዎች የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላውን ሊቃወሙ ይገባል›› አሉ፡፡
ዶክተር አብርሀም በዚህ መልእክታቸው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላው ማብቃት እንዳለበትና ጦርነትም መቆም እንደሚገባው አሳስበው ‹‹እናቶችም ልጆቻቸውን መቅበር ያቁሙ›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም የትግራይ ህዝብ ‹‹ልጆቼን አትውሰዱብኝ›› ከሚሉ እናቶች ጎን በመቆም ሰላምን እንዲመርጥና የልጆቻቸውን ደህንነት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዶክተር አብርሀም ይህንን መልእክት ያስተላለፉት በትግራይ ክልል ውስጥ በግዳጅ የሚደረገው ወታደራዊ ምልመላ ተጧጡፎ መቀጠሉን የሚያሳዩ የቪዲዮና የፎቶግራፍ መረጃዎች በስፋት መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

3 months ago