(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ ‹‹በእርግጠኝነት ሩሲያን እንበቀላታለን›› አሉ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በትላንትናው እለት በዋና ከተማቸው በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ቦታዎች ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግርም በሩሲያ ላይ ‹‹በእርግጠኝነት›› የበቀል እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ በቴሌግራም ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት ‹‹ትላንት በሩሲያ ጥቃት በተፈፀመባቸው 3 ቦታዎች ላይ አሁንም ህይወት የማዳን ፍለጋው ቀጥሏል፡፡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሾችን እየጠረጉ ቢሆንም እስካሁን 10 ሰዎች የት እንዳሉ አልታወቀም፡፡ በዚህ ጥቃት 30 ሰዎች መገደላቸው የተረጋገጠ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ፡፡›› ያሉት ዘለንስኪ ህፃናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውንም አስረድተዋል፡፡ ትላንት በኬይቭ ብቻም ሳይሆን በሌሎች ግዛቶች ውስጥም ድብደባ መከናወኑን ያስረዱት ፕሬዝደንቱ በክሪቪ ሪህ አንድ ጋራዥ፣ ሁለት ትምህርት ቤቶችና የመኖሪያ ህንፃዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና 7 ሰዎች እንቆሰሉ ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም በኬርሰን ግዛት ደግሞ አንድ ሆስፒታል በሚሳኤል መመታቱን ገልፀዋል፡፡ ሲያስረዱም ‹‹ሩሲያዊያን ምን ኢላማ እንዳደረጉ ያውቁ ነበር፡፡ በኬርሰን የመቱት ምንም ወታደራዊ ጠቀሜታ የሌለው ሆስፒታል ነው፡፡ በዚህም በሚያሳዝን ሁኔታ አንድ ዶክተር ሲገደል ሌላ ነርስ ቆስላለች፡፡ በሱሚ ግዛት ደግሞ በአንድ አፓርታማ ላይ ባደረሱት ጥቃት አንዲት እናትና ሴት ልጇን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል፡፡›› በማለት አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ የትላንቱን የሩሲያ ጥቃት አውግዘው ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዋና ፀሀፊው ጨምረውም ‹‹በየትኛውም ቦታ በሲቪሎችና ሲቪል መሰረተ ልማት ላይ የሚደረግ ጥቃት አለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን የሚጥስ በመሆኑ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል›› ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ካጃ ካላስ በዚህ ጥቃት የተነሳ በሩሲያ ላይ አዲስ ማእቀብ እንደሚጣል አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በዛሬ መልእክታቸው ሩሲያ ቀንና ለሊት በዩክሬይን ላይ ጥቃት ልትፈፅም እንደምትችል ገልፀው አጋሮቻቸው አስተማማኝ የአየር መቃወሚያ እንዲሰጧቸውም ጠይቀዋል፡፡

3 months ago