(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እሁድ ዕለት ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት መሠረት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸንፏል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳስታወቁት "ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድድር ከተካሄደባቸው 486 መቀመጫዎች ውስጥ 438ቱን አሸንፏል"።
ሰኔ አንድ ቀን የተካሄደው ይኸው የፓርላማ ምርጫ፣ በትግራይ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎችን ጨምሮ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ሳይካሄድ ቢቀርም፣ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ግን በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት ተከናውኗል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የብልጽግና ፓርቲ ጋር ከ40 በላይ ፓርቲዎች የተወዳደሩ ቢሆንም፣ አብዛኛዎቹ የፋይናንስ እጥረት የነበረባቸው በመሆኑ ገዥው ፓርቲ በ64 የምርጫ ክልሎች ውስጥ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ለብቻው ተወዳድሯል። ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በተሻለ ከፍተኛ የዕጩዎች ውክልና የነበረው ኢዜማ 293 ዕጩዎችን ሲያቀርብ፣ ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ 461 ዕጩዎችን ለውድድር አቅርቦ ነበር።
"የብልጽግና ፓርቲ ድል ውድድር ከተካሄደባቸው መቀመጫዎች ውስጥ ወደ 90 በመቶ የሚጠጋውን ይሸፍናል" ሲል የምርጫ ቦርድ በመግለጫው አብራርቷል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማው) ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሰይም በመሆኑ፣ ይህ አብላጫ የምርጫ ውጤት እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ በስልጣን ላይ ላሉት አብይ አህመድ ሀገሪቱን ለተጨማሪ አምስት ዓመታት በቢሮ ሆነው እንዲመሩ ሰፊ ዕድል የሚሰጣቸው ይሆናል።
ይሁን እንጂ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ የተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው ሳይካሄድ መታገዱ፣ እስካሁን እልባት ያላገኙ የውስጥ ግጭቶች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ እያሳደሩ ያለውን ከፍተኛ ጫና በጉልህ የሚያሳይ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

4 months ago