Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በየመን የጭነት መኪና ተገልብጦ የ4 ኢትዮጵያዊያን ህይወት ሲያልፍ ሌሎች 26 ቆሰሉ፡፡ ትላንት ሀሙስ በየመን አል ማሀራ በተሰኘ ግዛት ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ የ4 ኢትዮጵያዊያን ህይወት ማለፉ ተዘገበ፡፡

የመን ኦንላይን እንደዘገበው በተለምዶ ‹‹ዲና›› ተብሎ የሚጠራው የጭነት መኪና 58 ኢትዮጵያዊያንን አሳፍሮ ወደኦማን ድንበር በሚወስደው የበረሀ መንገድ እየተጓዘ ነበር፡፡ በመሀል ላይ መኪናው በመገልበጡ ከ4ቱ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ 26 መቁሰላቸውን የጠቀሰው ዘገባው ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ለህይወታቸው በሚያሰጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስረድቷል፡፡

ይህ አደጋ የደረሰበት መንገድ እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ብዙውን ጊዜ ህገወጥ ስደተኞችን ለማጓጓዝ ሹፌሮች የሚጠቀሙበት መሆኑንም ገልጿል፡፡ በመንገዱ ላይ በተደጋጋሚ አደጋ እንደሚደርስ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.