Logo
SeledaPost
በ25 ድምፅ ወደ ምክር ቤት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የድምፅ ቁጥር የተመረጡ ተፎካካሪ ዕጩዎች መኖራቸው ታወቀ!
 
ምርጫ ቦርድ ባወጣቸው ተከታታይ መግለጫዎች ያጸደቃቸው ከፊል ውጤቶች፣ በርካታ ተፎካካሪ በሌለባቸው የምርጫ ክልሎች የሚወዳደሩ የተቃዋሚ ዕጩዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የመራጮች ድምፅ ወደ ምክር ቤቶች መግባታቸውን አሳይተዋል።
 
ከእነዚህ መካከል ለድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት በኩርቱ የምርጫ ክልል የተመረጡት የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ዕጩ አቶ ጀማል ኡመር ኢብራሂም፣ ከተመዘገቡት 2,204 መራጮች መካከል ያገኙት ድምፅ 25 ብቻ (1% ገደማ) እንደሆነ ተገልጿል።

በጀሎበጂና የምርጫ ክልልም የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ተወካዩ አቶ ረመዳን መሐመድ ሰኢድ 200 ድምፅ (3%) ብቻ በማግኘት ወደ ምክር ቤት መግባት ችለዋል።ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በእነዚህ የምርጫ ክልሎች ከወንበሮቹ ቁጥር እኩል ከሆኑት ዕጩዎች ውጪ ሌላ ተወዳዳሪ ፓርቲ ባለመኖሩ ነው።
 
እስካሁን ከተመረጡት 8 ተቃዋሚዎች መካከል እውነተኛ የአብላጫ ድምፅ (ከ50% በላይ) ያገኙት የኦብነግ ተወካይ አቶ መሀሙድ ሀሰን (73%) እና የአብን ዕጩ አቶ ጣሂር መሀመድ (59%) ብቻ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 6ቱ ዕጩዎች የኢዜማውን መሪ አቶ እዮብ መሳፍንትን (42%) ጨምሮ ከ50% በታች ድምፅ አግኝተዋል።ስምንቱም የተቃዋሚ ወኪሎች ያሸነፏቸው ወንበሮች ብልፅግና ፓርቲ ውክልናን ለማሳደግ በሚል ሆነ ብሎ ዕጩ ያላቀረበባቸው መሆኑ ታውቋል።
ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Seledadotio
Seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.