Logo
SeledaPost
በኢትዮጵያ  የጫት ተጠቃሚነት መጠን መጨመር አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የጫት ተጠቃሚነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ለአዕምሮ ጤና ትልቅ ስጋት መሆኑ ተነግሯል።

በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማዉ እንደገለጹት፤ የጫት ተጠቃሚነት ቁጥር ከፍ ማለት አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በአንጻሩ የአልኮል እና የሲጋራ ተጠቃሚነት አዲስ በወጡ የቁጥጥር ህጎች ምክንያት መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የሱስ ችግር ከአንጎል ባዮሎጂ ጋር በቀጥታ የተያያዘ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የሚመለከታቸው አካላትም በጫት ቁጥጥር ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል።

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምናን ከሌሎች የህክምና አይነቶች ጋር አቀናጅቶ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምናን በዘመናዊ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ 1መቶ45 የመኝታ አልጋዎችን አዘጋጅቶ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ሆስፒታሉ ከአማኑኤል ሆስፒታል ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመኝታ አልጋ ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር እስጢፋኖስ፤ አገልግሎቱም ለህጻናት፣ ለአዋቂዎች፣ ለአረጋውያን እና ከሱስ ጋር የተያያዙ ችግሮች ላለባቸው ወገኖች በተለያዩ ክፍሎች ተለይቶ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

Seledadotio
Seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.