ከስታዲየም በሮች እስከ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መድረኮች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፖርት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ሕይወቱና የሩብ ክፍለ ዘመን የሙያ ስኬቱ ሆኗል።
ከስታዲየም በሮች የጀመረው ጉዞው እስከ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መድረኮች ዘልቋል።
በሀገር ውስጥ ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለው "ሀትሪክ ስፖርት" አዘጋጅ የሆነው ይስሐቅ በላይ፥ በሙያው ከ24 ዓመታት በላይ የዘለቀ ልምድ አካብቷል።
ጋዜጠኛ ይስሐቅ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበረው ቆይታ ወደ ስታዲየም መግባት ያልቻለ አካል ጉዳተኛን እየገፋ በማስገባት የስፖርት ሕይወት መነሻውን እንዳደረገ ይናገራል።
በአፍሪካ ብሎም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ተዘዋውሮ ሙያዊ ልምዶችን የቀሰመ ሲሆን፥ ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር ፊፋ ጋር ከ15 ዓመታት በላይ የዘለቀ ሙያዊ ግንኙነት መፍጠር ችሏል።
የዓለም ኮከብ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾችን በመምረጥ ሂደትም ለ8 ዓመታት ያህል ተሳታፊ እንደነበር ገልጿል።
አራት የዓለም ዋንጫ መድረኮችን በአካል መታደሙን የገለጸው ይስሐቅ ዘንድሮም በስፖርቱ ዓለም በጉጉት የሚጠበቀውን የዓለም ዋንጫ ለመታደም ተዘጋጅቷል።
በዘንድሮው ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ ውድድር ስፔን እና ፈረንሳይ ለፍፃሜው ይደርሳሉ የሚል ሙያዊ ግምቱንም አስቀምጧል።
የሦስት ልጆች አባት የሆነው ይስሐቅ በላይ፥ "ሀትሪክ ስፖርት"ን እንደ አራተኛ ልጁ እንደሚመለከተው በመግለጽ ለስፖርት ያለውን ፍቅር አውስቷል።
ከስታዲየም በሮች የተነሳው የሙያ ጉዞው ዛሬ የኢትዮጵያን ስም ይዞ በዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መድረኮች ላይ እንዲታደም አድርጎታል።
በበጸሎት መንገሻ
የሀትሪክ ስፖርት አዘጋጅ ይስሐቅ በላይ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረገውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://youtu.be/y0bKkD406...

4 months ago