(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ፣ ሀገሪቱ ተጨማሪ 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት እና የሶስተኛ ቴሌኮም ኦፕሬተር ወደ ገበያው መግባት በእጅጉ እንደሚያስፈልጋት ተጠቆመ። የቀድሞው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአሁኑ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዋና ኃላፊ ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የዘርፉን መዋቅራዊና መሰረተ ልማታዊ ክፍተቶች በግልጽ አብራርተዋል። ሀገሪቱ ለያዘችው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይ መሳካት፣ የቴሌኮም ማማዎችን ቁጥር አሁን ካለበት በሶስት እጥፍ ማሳደግ የግድ እንደሚልም አሳስበዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማት ከሕዝብ ቁጥሩ አኳያ ሲመዘን እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ኃላፊው በቁጥራዊ መረጃ ሞግተዋል። ለምሳሌ ያህል፣ አንጋፋው ኢትዮ ቴሌኮም ወደ 10 ሺሕ የሚጠጉ ማማዎች ያሉት ሲሆን፣ ሳፋሪኮም በበኩሉ 3,500 ማማዎች አሉት። ከሳፋሪኮም ማማዎች ውስጥ 40 በመቶ የሚሆኑት ከኢትዮ ቴሌኮም የተከራያቸው ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹን ደግሞ ራሱ የገነባቸው ናቸው። በአጠቃላይ የሁለቱም ኦፕሬተሮች የቴሌኮም ማማዎች ድምር ከ15 ሺሕ በታች ነው። በጎረቤት ሀገራት ካለው የማማ እና የሕዝብ ቁጥር ንጽጽር አንጻር ሲታይ ይህ ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ አሁን ካላት የሕዝብ ብዛት አኳያ ተጨማሪ 30 ሺሕ አዳዲስ ማማዎች ያስፈልጓታል። ይህንን ግዙፍ ክፍተት ለመሙላት ደግሞ የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት (PPP) ወሳኝ ሚና እንዳለው ዶክተር አንዱዓለም አስረድተዋል።
ከዚህም ባሻገር፣ በቴሌኮም ዘርፉ ላይ መሠረታዊ የፖሊሲ እና የአሠራር ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ ባለሙያው ክሪቲካል የሆነ ሐሳብ ሰንዝረዋል። እስካሁን ባለው አሠራር የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የመሰረተ ልማት ግንባታውንም ሆነ የቴሌኮም አገልግሎት አቅርቦቱን አጣምረው እየሠሩ ይገኛሉ። ይህ አሠራር ኦፕሬተሮችን ከዋናው ተልዕኳቸው እንዲዘናጉ እንደሚያደርጋቸው ኃላፊው ያምናሉ። በመሆኑም፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን (ማማዎችን) ብቻ የሚገነቡ ገለልተኛ ኩባንያዎች ፈቃድ አግኝተው ወደ ገበያው ሊገቡ ይገባል። ይህ አሠራር ቢተገበር፣ ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ኦፕሬተሮቹ ማማዎቻቸውን ለእነዚህ ገለልተኛ ኩባንያዎች በመሸጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የካፒታል ገንዘብ ማሰባሰብ ይችላሉ። አዳዲሶቹም ሆነ ነባሮቹ ኦፕሬተሮች ማማ ከመገንባት ውጣ ውረድ ተላቀው፣ ከመሰረተ ልማት አቅራቢዎች ማማዎቹን እየተከራዩ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ሲሉ ተንትነዋል።
ወደ ሀገሪቱ የገባው ሁለተኛው ኦፕሬተር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ለቴሌኮም ፈቃድ ከከፈለው 850 ሚሊዮን ዶላር እና ለኤም-ፔሳ (M-Pesa) ፈቃድ ካወጣው 50 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ፣ እስካሁን በሥራ ማስኬጃ እንቅስቃሴዎች ላይ ብቻ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ መዋዕለ ንዋይ አፍስሷል። ኩባንያው ባለፉት ሶስት የሥራ ዓመታት ውስጥ 12 ቢሊዮን ብር ግብር ለመንግሥት ገቢ አድርጓል። የዘርፉን ዕድገት ይበልጥ ለማፋጠንና ጤናማ ፉክክር ለመፍጠር የሶስተኛ ኦፕሬተር መግባት ቁልፍ መሆኑ ቢታመንም፣ በሁሉም ኦፕሬተሮች መካከል ፍትሐዊ የውድድር ሜዳ መኖሩን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት። ለዚህም ሲባል፣ የኢትዮጵያ የኢንተርኔት መለያ ጎራ (ዶሜይን - .et) በአንድ ኦፕሬተር ሥር ከመሆን ይልቅ፣ ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ በሆነ ተቆጣጣሪ አካል ሥር ሊተዳደር እንደሚገባ ዶክተር አንዱዓለም በአጽንዖት አሳስበዋል።

5 months ago