(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአውስትራሊያ መከላከያ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርለስ፣ ሀገራቸው በፈረንሳይ እና ብሪታንያ በሚመራውና "በጥብቅ መከላከል ላይ ብቻ ባተኮረው" የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ የንግድ መርከቦች ደህንነት ማስጠበቅ ተልዕኮ ላይ እንደምትቀላቀል ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ከ40 ሀገራት ተወካዮች ጋር ከተወያዩ በኋላ እንዳስታወቁት፣ አውስትራሊያ ከዚህ ቀደም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ከኢራን የድሮን ጥቃቶች ለመከላከል በቀጠናው አሰማርታው የነበረውን 'ዌጅቴይል ኢ-7ኤ' የተሰኘ የስለላ አውሮፕላን ለዚህ አዲስ ተልዕኮ ታበረክታለች።
ማርለስ ባወጡት መግለጫ "አውስትራሊያ በዩናይትድ ኪንግደም እና በፈረንሳይ የሚመራውን፣ ገለልተኛ እና የመከላከል ዓላማ ብቻ ያለውን የብዝሃ-ሀገር ወታደራዊ ተልዕኮ እንደተቋቋመ ለመደገፍ ዝግጁ ናት" ብለዋል። አክለውም፣ ይህ ተልዕኮ ሀገራቸው "ለአለም አቀፍ ንግድ ደህንነት መረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት" ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
ይህ የአውስትራሊያ እና የአውሮፓ ሀገራት እርምጃ የመጣው፣ አሜሪካ በኢራን ላይ በከፈተችው የማጥቃት ዘመቻ የኔቶ አባል ሀገራት አልተባበሩኝም በሚል ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ትችት እየቀረበባቸው ባለበት ወቅት ነው። ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ከጦርነቱ በኋላ ባህረ ሰላጤው ለንግድ መርከቦች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ክፍት ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ ሀገራትን በማስተባበር ጥምረት በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፈው ሳምንት እንደተናገሩት፣ የአሜሪካ ጦር የንግድ መርከቦችን ከፋርስ ባህረ ሰላጤ በሰላም በማጀብ የማውጣት ዘመቻውን ማቋረጡን ተከትሎ፣ ስለ አዲሱ የጥበቃ ተልዕኮ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር እንደሚወያዩ ጠቁመው ነበር።

5 months ago