በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ57 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ስምምነት ተፈጽሟል - አቶ መላኩ አለበል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በ4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ57 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ስምምነት ተፈጽሟል አሉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሐሳብ ለ6 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
አቶ መላኩ አለበል ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኤክስፖው ከ350 በላይ ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈዋል።
162 ሺህ 154 ሰዎች በጎበኙት ኤክስፖ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ 20 ስታርት አፖች የፈጠራ ስራቸውን ለጎብኝዎች አቅርበዋል ብለዋል።
አዳዲስ ፈጠራ የተጨመረባቸው የምርት ልማት ውድድሮች በ22 ኢንዱስትሪዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን፤ በምግብ ቅምሻ 10 ድርጅቶች ከተለያዩ ግብዓቶች ያመረቷቸውን ምርቶች በተሳታፊዎች ማስመረጣቸውን ገልጸዋል።
ከ12 ሺህ በላይ የግብይት ትስስሮች በአምራቾች መካከል መፈጸማቸው የኤክስፖው ስኬት እንደነበረ አመልክተዋል።
በተጨማሪም ከ57 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ስምምነት መፈጸሙን፣ በ7 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዓለም አቀፍ ሴሚናሮች መካሄዳቸውን እና የመንግሥትን ፖሊሲ ለግሉ ዘርፍ ትርጉም ባለው መልኩ ማስተዋወቅ መቻሉን አብራርተዋል።
በለይኩን ዓለም

28 days ago