የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2014 ዓ.ም “ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ” ከመጀመሩ በፊት እንደ ሀገር ኢንዱስትሪዎች በዓይነትም ሆነ በቁጥር አነስተኛ ነበሩ አሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 25 "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሐሳብ የተከፈተው 4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በድምቀት ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።
ተኪ ምርቶችን በዓይነት፣ በጥራትና በብዛት ማምረት የውጭ ምንዛሪ ወጪን ከማስቀረት ባለፈ የዘርፉን አቅም መገንባት የዘመኑ አርበኝነት ተደርጎ ይወሰዳልና ሁነቱ በዘንድሮው የአርበኞች በዓል ላይ ማረፉ ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ ሆኗል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት÷ ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በፊት እንደ ሀገር የነበሩት ኢንዱስትሪዎች አነስተኛ ነበሩ።
የነበሩት ኢንዱስትሪዎችም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት በምርት ሂደት መስተጓጎላቸው እና በሰሜኑ ጦርነት የጥቃት ኢላማ መሆናቸው ትልቅ ጫና እንደነበር አንስተዋል።
ከዚያ መንገድ ለመውጣት እና አዲስ መንገድ ለመከተል የ“ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ” መጀመሩን ያስታወሱት ሚኒስትሩ÷ የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያግዝ ሰነድ ቀርቦ ውይይት በመደረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ድጋፍ ማግኘቱን አመልክተዋል።
በዚህም በንቅናቄው "በኢትዮጵያ ዲዛይን ተደርገው፣ በኢትዮጵያ ተመርተው እና ተገጣጥመው ለሥራ የቀረቡ ማሽኖችን ወደምናይበት ምዕራፍ ተሸጋግረናል" ብለዋል።
ሚኒስትሩ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇
https://www.youtube.com/wa...

29 days ago