Logo
FBC
ፒኤስጂ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፒኤስጂ በድምር ውጤት ባየርን ሙኒክን በማሸነፍ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደርሷል።

ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተደረገው የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ እና ባየርን ሙኒክ 1 ለ 1 ተለያይተዋል።

የፒኤስጂን ግብ ኦስማን ዴምቤሌ ጨዋታው በተጀመረ ሶስተኛ ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር፤ የባየርን ሙኒክን የአቻነት ግብ ሃሪ ኬን ከመረብ አሳርፏል።

በዚህም ፒኤስጂ በድምር ውጤት 6 ለ 5 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በቅቷል።

የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ ለተከታታይ የውድድር ዓመት ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ትናንት አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን ማረጋገጡ ይታወቃል፡፡

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.