(ዘ-ሐበሻ ዜና) የምርመራ መዝገብ ተዘግቶ ነገ የክስ መስማት ሂደት ይጀመራል። የፌንቴክ (Fintech) ኢንቨስትመንት ማጭበርበር ድርጊት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬና ግብረ አበሮቹ የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ሂደታቸውን ጨርሰው ነገ በይፋ ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑ ታውቋል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲካሄድ የነበረው የምርመራ መዝገብ ተጠናቆ በአራዳ ፍርድ ቤት የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚያበቃ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ የክስ መዝገቡን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ነገ እንደሚያቀርብ ተረጋግጧል። አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተለያዩ ከባድ የወንጀል ክሶችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን መተላለፍ የሚለው ክስ በዋነኝነት እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችሏል።
ነገ በሚካሄደው የችሎት ውሎ አቃቤ ህግ ክሱን ለፍርድ ቤቱ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም የተከሳሾችን ማንነት በዝርዝር ካረጋገጠ በኋላ ክሱ በጽሁፍ ደርሷቸው እንዲያነቡት ያደርጋል። ተከሳሾቹም በቀረበባቸው ክስ ላይ ከጠበቆቻቸው ጋር ተነጋግረው መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡና እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ጨምሮ ሌሎች ቅሬታዎች ካሏቸው እንዲያቀርቡ እድል እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል። በነገው የችሎት ሂደት ተከሳሾች የዋስትና መብት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም የዋስትና ጥያቄውንና የክስ መቃወሚያውን ሰምቶ ውሳኔ ለመስጠት ወይም ተለዋጭ ክርክሮችን ለመስማት ሌላ ቀጠሮ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል። ይህ የሰራዊት ፍቅሬ ክስ በሀገሪቱ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ ካሉ የማጭበርበር ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ትልቅ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ በመሆኑ የነገው የችሎት ውሎ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

5 months ago