Logo
FastMereja
በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ኦክሎክ ሞተርስ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ

​በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የ«ኢትዮጵያ ታምርት» ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ኦክሎክ ሞተርስ፣ በኤክስፖው መርሃ-ግብር ወቅት የሚቆይ የተሽከርካሪዎች ዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

​በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ የተከፈተውና ካለፈው ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን ድረስ የሚቆየው ብሔራዊ ኤክስፖ በርካታ አምራቾችንና የኢንዱስትሪ ተቋማትን እያሳተፈ ይገኛል።

​በሀገር ውስጥ ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም ዘርፍ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የቆየውና የሦስት መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ባለቤት የሆነው ኦክሎክ ሞተርስ፣ በኤክስፖው ላይ ከ13 በላይ የተለያዩ የተሽከርካሪ ሞዴሎችን ይዞ መቅረቡን የድርጅቱ ተወካዮች ገልጸዋል።

​ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በገበያው ላይ በስፋት የሚንቀሳቀሱትን የውሊንግ (Wuling) ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ለቤተሰብ፣ ለታክሲ አገልግሎት፣ ለድርጅቶች ሰርቪስ እንዲሁም ለጭነትና ለካርጎ አገልግሎት የሚውሉ ፒክአፖችንና ቫኖችን ማቅረቡን አስታውቋል።

​የሽያጭ ሂደቱንና የተጠቃሚዎችን አቅም በተመለከተ ከድርጅቱ ተወካዮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ፍላጎት ያላቸው ደንበኞች ክፍያውን በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) መፈጸም የሚችሉ ሲሆን፣ በተለዋጭ አማራጭ ደግሞ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ከ30% እስከ 50% የሚሆነውን ቅድመ ክፍያ በመክፈል ተሽከርካሪዎቹን በብድር መውሰድ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን አስረድተዋል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.