የኢንዱስትሪ ዘርፉን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት የሚያግዝ ህግ እየተዘጋጀ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ የሚስተዋለውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት የሚያግዝ ህግ እየተዘጋጀ ነው አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት 4ኛውን ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት፥ የፋይናንስ ተቋማት ለኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚያቀርቡት ብድርና ድጋፍ አነስተኛ መሆኑ ተገምግሟል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት ከሀገሪቱ ሀብት ምንያህሉ ወደ ኢንዱስትሪ መፍሰስ እንዳለበት የሚወስን ህግ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፥ ይህም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
ይህ ህግ የግልም የመንግስትም ባንኮችን የሚመለከት ሲሆን፥ የኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚገባውን ድርሻ እንዲያጣ ያደረጉ ሰው ሰራሽ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
ነገር ግን ብዙ ሀብት ካልፈጠርን አሁን ያለው ሀብት በቂ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሀብት ለሁሉም ዘርፎች ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ለመፍጠር ሁሉም ነገር ንግድና ኮንትሮባንድ ብቻ እንዳይሆን በህግ እንደሚቀየር አስረድተዋል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ

1 month ago