ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ አስደናቂ ሥራዎችን እያከናወነች ነው - ሪቻ ዳቩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ አስደናቂ ተግባራትን እያከናወኑ ነው አሉ የካሜሩን የዳያስፖራና ዜግነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ሪቻ ዳቩ፡፡
ዳይሬክተሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ትላልቅ ርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች ብለዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት እየተከናወኑ የሚገኙት እነዚህ ተግባራት የልማት አጋሮችን አስተዋጽኦ የሚያሳድጉ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው እድገት ላይ የሚኖራቸውን ሚና እንደሚያጠናክር አስረድተዋል፡፡

5 months ago