Logo
YenetaTube
ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ - የጥያቄና የትምህርት ቀን 🙏

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ በዕለተ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠው ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ዕለተ ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ አንድም በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ ዕለቱ “የትምህርት ቀን” ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር፣ ሲጠይቅ መሰንበት እንደሚገባው ይህ መጽሐፋዊ ሥርዓት ይነግረናል፡፡ በዕለተ ሰኞ የነጋዴዎችን ንብረት መገልበጥና ማባረሩን መነሻ በማድረግ “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ?” ሲሉ ጠይቀውታል፡፡ ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራት፣ ድንቅ ድንቅ ሥራዎችና ትምህርቱ ህዝቡ እንዲከተለው ስላደረገ የካህናት አለቆች በቅናት ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ሊያጋጩት የቀየሱት ስልት ነው፡፡

ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነውና ጌታችን በራሴ ሥልጣን ነው ቢላቸው ጸረ መንግሥት ነው በማለት ለሮማ መንግሥት ያሳጡት ነበር፡፡ ጌታችን ግን ለጥያቄያቸው ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?” በማለት በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ እነርሱም “ከሰማይ ነው” ቢሉት “ለምን አላመናችሁበትም?” እንዳይላቸው ሰጉ፡፡ “ከሰው ነው” ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ መምህር ይፈሩት፣ እንደ አባት ያከብሩት ነበርና እንዳይጣሏቸው ፈሩ፤ እናም “ከወዴት እንደሆነ አናውቅም” የሚል የተንኮል ምላሽ ሰጡት፡፡ እርሱም “እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው፡፡ በልቡናቸው የሚያደርጋቸውን ተግባራት ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንደሚያደርግ ቢያውቁም በክፋትና በጥርጥሬ ስለተሞሉ ነበር የጠየቁት፡፡

በማቴዎስ ወንጌል 21÷28፣ 25÷46፣ በማርቆስ ወንጌል 12÷12፣ 13÷37፤ በሉቃስ ወንጌል 20÷9፣ 21÷38፣ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለማክሰኞ ዕለት የሚነገሩ ትምህርቶችን ይዘዋል፡፡ ዳግመኛም በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ፣ ከዋዛ ፈዛዛ ተጠብቆ የጌታችንን ውለታ፣ ሕማሙን፣ ግረፋትና ስቅለቱን፣ ሞቱንና መከራውን እያሰበ በስግደት ይህን ሳምንት ሊያሳልፈው ይገባል፡፡ ገዳማውያን ይህን ፍቅሩን እያሰቡ በጾምና በጸሎት ይኖራሉ፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.