ትራምፕ ለኢራን የ48 ሰዓት ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡ “ሁሉም ነገር ወደ ገሃነም ይቀየራል”
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በአስቸኳይ ካልተከፈተ ወይም የሰላም ስምምነት ካልተደረሰ በኢራን ላይ “ገሃነም ይዘንባል” ሲሉ አስጠነቀቁ።
ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ቀደም ሲል ለኢራን የሰጡት የ10 ቀናት የጊዜ ገደብ እያበቃ መሆኑን ገልጸው፣ አሁን የቀረው 48 ሰዓት ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል።
“ለኢራን ስምምነት እንድታደርግ ወይም የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን እንድትከፍት የ10 ቀን ጊዜ ሰጥቻት የነበረውን ታስታውሳላችሁ? አሁን ጊዜው እያለቀ ነው—በእነሱ ላይ ገሃነም ከመውረዱ በፊት 48 ሰዓታት ብቻ ቀርተዋል” ብለዋል ትራምፕ።
ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው በኢራን ምዕራባዊ ክፍል አንዲት የአሜሪካ ኤፍ-15 (F-15E) ተዋጊ ጄት መመታቷን ተከትሎ ውጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት ወቅት ነው። ፕሬዝዳንቱ ኢራን የባህር ወሽመጡን ካልከፈተች የኃይል እርምጃ እንደሚወስዱ ደጋግመው ሲዝቱ ቆይተዋል።
የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለዓለም የነዳጅ ንግድ ቁልፍ መተላለፊያ ሲሆን፣ መዘጋቱ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
የትራምፕ አስተዳደር ኢራን የቀረበላትን የ15 ነጥብ የሰላም ጥያቄ እንድትቀበል ግፊት እያደረገ ሲሆን፣ የጊዜ ገደቡ እስከ ሰኞ ምሽት (እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዝያ 6 ቀን 2026) ድረስ ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል።
seledadotio

6 months ago
Subscribe to Unlock
For 100$ / Monthly