Logo
SeledaPost
ብጉር | Acne vulgaris

✔️ ብጉር በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቅ፤ ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው።

✔️ብጉር ከጨቅላ ህጻናት ጀምሮ የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ከ12-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ይታያል።

✔️ ብጉር አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከወጣትነት የእድሜ ክልል በኋላ (30 እና 40ዎቹ) የሚከሰተው የብጉር አይነት ግን በብዛት ሴቶች ላይ ይታያል።

➡ ለብጉር መከሰት አራት መሰረታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ናቸው
  
1- Follicular hyperkeratinization; ይህም የሞቱ ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ እንዲዘጋ ያደርጋል
  
2-የወዝ በብዛት መመረት (increased sebum production)

3-Propionibacterium acne የሚባለው የባክቴሪያ አይነት

4-ብግነት (Inflammation)

➡ ብጉርን እና ብጉር መሰል ሽፍታዎችን (Acneiform eruption) የሚያባብሱ ነገሮች

✍ጭንቀት (stress)
✍ከመጠን ያለፈ ውፍረት
✍በወር አበባ አካባቢ
✍የሚዋጡም ሆነ የሚቀቡ መድሀኒቶች (steroids, phenytoin...)
✍በስራ ሁኔታ የሚያጋጥሙ ኬሚካሎች

✍በቆዳችን ላይ በሚከሰተ መፈጋፈግ (friction) ወይም ጫና (pressure) ፤ ለምሳሌ በህመም ሆነ በሌላ ምክንያት ለረጅም ግዜ በጀርባው የሚተኛ ሰው ጀርባው ላይ ብጉር ሊወጣ ይችላል ወይም የጡት ማስያዣ ገመድ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ ሊወጣ ይችላል 
✍ ለረዥም ሰአት የፊት ማስክ ማድረግ
✍በውስጣቸው comedogenic ingredients የያዙ የፊትና የጸጉር ቅባቶች

➡ ብጉር እንዴት ይታከማል?

✔️ ብጉር በአብዛኛው ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቆዳ ህመም በመሆኑ በራሱ የሚጠፋውም ከእድሜ ጋር ተያይዞ ነው ፤ ስለዚህም ምልክቶቹን መቆጣጠር እንጅ በህክምና ማዳን (በአንድ ህክምና እስከ መጨረሻው እንዳይመጣ ማድረግ) አይቻልም።
    
በዚህም ምክንያት የብጉር ህክምና ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ታካሚዎች ከቆዳ ሐኪማቸው ጋር እየተመካከሩ ህክምናውን መከታተል ይኖርባቸዋል።

✔️ እዚህ ጋር ብጉር በራሱ ጊዜውን ጠብቆ የሚጠፋ ከሆን መታከም ለምን ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ፤ብጉር ከሚያሳድረው የስነ-ልቦና ጫና በተጨማሪ ሳይታከም በቆየ ቁጥር ፊታችን ላይ ጠባሳ የመፍጠር እድሉ የሰፋ ስለሆነ በጊዜ መታከሙ ይመከራል።

✔️ የብጉር ህክምና እንደ ጥንካሬው መጠን በሚቀባ ፣ በሚቀባና በሚዋጥ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ሊታከም ይችላል

✔️ ከዋናው ህክምና በተጨማሪ በውስጣቸው Salicylic acid, Benzyle peroxide የያዙ መታጠቢያ ሳሙናዎች መጠቀም ያስፈልጋል

➡ ከህክምናው በተጨማሪ ማድረግ የሚጠበቅብን

👉እንቅስቃሴ ማድረግ (ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳል)
👉ብጉሮቹን ለማፍረጥ አለመሞከር (ጠባሳ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ)
👉ለቆዳ ጤና መጠበቂያም ሆነ ለውበት የምንጠቀማቸው ምርቶች Oil-free & non-comedogenic መሆናቸውን ማረጋገጥ
👉ፀሐይ መከላከያ (sun-screen) መጠቀም (መጠቀም ያለብን የፀሐይ መከላከያ እንደ ቆዳችን አይነት ስለሚለያይ የቆዳ ሐኪም ያማክሩ)
👉ቆዳችን ላይ ጫና (pressure) የሚፈጥሩ ነገሮችን (helmets, ስልክ, የቦርሳ/የጡት ማስያዣ ገመድ, የፊት ማስክ) መቀነስ
👉ሰውነታችንን ካላበን መታጠብ

✔️ በመጨረሻም ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል

seledadotio
seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.