ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የሰው ልጅ ዳግም ወደ ጨረቃ ጉዞ
የሰው ልጅ በጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ድንቅ ክስተት ዛሬ ተመዝግቧል።
ከአምስት አስርተ ዓመታት በላይ ለሚሆን ረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የሰው ልጆች ወደ ጨረቃ የመጓዝ ጉዞ በአርቴሚስ 2 መንኮራኩር አማካኝነት ዳግም ህያው ሆኗል።
አራት ጠፈርተኞችን አሳፍራ ወደ ጨረቃ መንደርደሯ የተሰማው ይህቺ መንኮራኩር የሰው ልጅ ወደ ማርስ ለሚያደርገው ቀጣይ ጉዞ እንደ ትልቅ መነሻ ተደርጋ ተወስዳለች።
ይህ ታሪካዊ ጉዞ በጠፈር ምርምር ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ስኬት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂው ረገድ ያለውን እመርታ ለዓለም ያሳየ ክስተት ነው።
አራቱ ጠፈርተኞች ጨረቃን በመዞር የሚያደርጉት ይህ ተልዕኮ ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነ በመሆኑ በመላው ዓለም የሚገኙ የሳይንስ አፍቃሪዎችን ቀልብ ስቧል።
መንኮራኩሯ በተሳካ ሁኔታ ወደ ህዋ መተኮሷን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች እና ተመራማሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ ዋና ዓላማ የሰው ልጅ በጨረቃ ምህዋር ውስጥ በሰላም ተጉዞ መመለስ የሚችልበትን ሁኔታ በዝርዝር ማጥናት ሲሆን ይህም ለወደፊቱ በጨረቃ ላይ ቋሚ የሰው ልጆች መኖሪያ ለመመስረት ለታለመው እቅድ መሰረት የሚጥል ነው።
seledadotio

4 months ago