''የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ኬብል እና የአየር መንገድ በረራዎቿ ሳይቀር በጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው'' ተባለ
📌በድሬዳዋ ከተማ ተጽዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ሚዲያ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል
#ethiopia | የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር «የሰላም ቱሪዝም ለሀገር ግንባታ» በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ፣ የሀገር ውስጥ ሰላም እና የባህር በር ባለቤትነት ለኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸው ተገለጸ።
ተጽዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ሚዲያ አካላትን እና ልዩ ልዩ ተሳታፊዎችን ባካተተው በዚህ መድረክ ላይ ጽሑፍ ያቀረቡት ጋዜጠኛ ብስራት መለሰ ፣ የሀገረ መንግስት ግንባታ (Nation Building) በተለያዩ ብሔሮች እና ማንነቶች መካከል ጠንካራ መስተጋብርን በመፍጠር ብሔራዊ ማንነትን የማጽናት ሂደት መሆኑን ገልጸዋል።
ጋዜጠኛው በማብራሪያቸው፣ የማንነት እና የፖለቲካ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ብቻ ህመም እንዳልሆኑ በማንሳት፤ እንደ ስፔን ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ካሜሩን እና ጀርመንን የመሳሰሉ ሀገራት ተመሳሳይ ፈተናዎች እንዳሉባቸው ጠቅሰዋል።
ይሁንና እነዚህን ውስጣዊ ጥያቄዎች በውይይት፣ በመደማመጥ እና በድርድር መፍታት ሲገባ በጥይት ለመመለስ መሞከር ለነገ የሚተርፍ ተጨማሪ ቁስል እና ለአብሮነት አደጋ የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።
"ያለ ሰላም ሀገር አይገነባም" ያሉት አቅራቢው፣ ግጭት መፍረስን እና መለያየትን ብቻ እንደሚያመጣ አስረድተዋል።
በመድረኩ ላይ በስፋት ከተነሱት አበይት ጉዳዮች መካከል የቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ እና የባህር በር ጥያቄ ይገኝበታል።
አሁን ላይ ዓለም አቀፉ ሥርዓት ከተቋማዊ የጋራ ውሳኔ (Collective Decision) አሰራር ወጥቶ ወደ "ሪያሊዝም" (የኃይል ሚዛን እና ብሔራዊ ጥቅም ትግል) ማዘንበሉን ያነሱት ጋዜጠኛ ብስራት፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ቀጠና የተፈጠረው የኃያላን ሀገራት ፉክክር ለቀጠናው ስጋት መሆኑን አመላክተዋል።
እንደ ጋዜጠኛው ገለጻ፣ ጅቡቲን ጨምሮ በቀጠናው በርካታ የውጭ ሀገራት የጦር ሰፈሮቻቸውን መገንባታቸው እንዲሁም የተለያዩ የሽብር ቡድኖች መንቀሳቀሳቸው አካባቢውን ውስብስብ የጦር ቀጠና አድርጎታል። በዚህ ውጥረት ውስጥ የባህር በር አልባ መሆን ህልውናን ለሌሎች አሳልፎ ከመስጠት ተለይቶ እንደማይታይ አበክረው ገልጸዋል።
"የባህር በር ማጣት ኢኮኖሚያዊ ጫና ብቻ ሳይሆን የህልውና ጥያቄ ነው" ያሉት አቅራቢው፣ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ኬብል እና የአየር መንገድ በረራዎቿ ሳይቀር በጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሙሉ ሉዓላዊነቷ አደጋ ላይ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች (ለምሳሌ እስከ 2,000 ኪ.ሜ የሚምዘገዘጉ) መኖራቸው የጸጥታ ስጋት መሆኑን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ የንግድ መርከቦቿን ደህንነት ለመጠበቅም ሆነ ቀጠናዊ ስጋቶችን ለመቋቋም በባህር ላይ መገኘት ግድ እንደሚላት አብራርተዋል።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ ይህንን የባህር በር ጉዳይ አስተማማኝ እስካላደረገች ድረስ ሉዓላዊነቷ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል ገልጸዋል።
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽን
ያፌት ገ/ህይወት
ከድሬዳዋ
photo credit : Visit Oromia

7 months ago