Logo
FastMereja
ቅዱስ ጊዮርጊስ ለሼህ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ያላቸውን ጥልቅ ክብር ገለጹ

​#fastmereja I የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ለክለቡ ህልውና እና ስኬት ተወዳዳሪ የሌለው ውለታ ለዋሉለት ለታዋቂው ባለሀብት ለሼህ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ልዩ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ።

​ደጋፊዎቹ በመልዕክታቸው እንደገለጹት፤ ሼህ መሐመድ ያለምንም የግል ጥቅም ፍላጎት፣ ያላቸውን ሀብት ለክለቡ ውጤታማነት በማዋል ደጋፊው በርካታ የደስታ ጊዜያትን እንዲያሳልፍ አድርገዋል። በተለይም ክለቡ አሁን ላይ ባለበት አስቸጋሪ ወቅት "አለሁላችሁ" በማለት በድጋሚ ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑ ተጠቅሷል።

​"ውለታዎን ታሪክ አይዘነጋውም፤ እኛም ጊዮርጊሳውያን በሚገባ እናስታውሰዋለን" በሚል የቀረበው ይኸው መግለጫ፣ ባለሀብቱ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት በተለይም ለፈረሰኞቹ ክለብ ያደረጉት አስተዋጽኦ በታሪክ ማህደር ደምቆ የሚቀመጥ መሆኑን ያመላክታል። ሼህ መሐመድ አል-አሙዲ ለዓመታት የክለቡ የጀርባ አጥንት በመሆን ከፍተኛ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.