Logo
FIDEL POST NEWS
አርሰናል፣ ፒኤስጂ እና ሪያል ማድሪድ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ አለፉ

​በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታዎች አርሰናል፣ ፒኤስጂ እና ሪያል ማድሪድ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው መሸጋገራቸውን አረጋግጠዋል።

​አርሰናል በሜዳው ባየር ሌቨርኩሰንን ያስተናገደ ሲሆን፣ በኤዜ እና ዴክላን ራይስ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል።

በመጀመሪያው ጨዋታ 1 ለ 1 ተለያይተው የነበረ ቢሆንም፣ መድፈኞቹ በድምር ውጤት 3 ለ 1 በማሸነፍ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

​ፒኤስጂ በበኩሉ ወደ ለንደን አቅንቶ ቼልሲን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። ክቫራትስኬሊያ፣ ባርኮላ እና ማዩሉ ግቦቹን ያስቆጠሩ ሲሆን፣ የፈረንሳዩ ክለብ በድምር 8 ለ 2 በሆነ አስገራሚ ውጤት ተከታዩን ዙር ተቀላቅሏል።

​በእንግሊዝ በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በርናርዶ ሲልቫ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱን ተከትሎ ቪኒሲየስ ጁኒየር ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማድሪድን ድል አብስሯል።

ሲቲ በሀላንድ አማካኝነት ግብ ቢያስቆጥርም፣ ሪያል በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው ገብቷል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.