Logo
FIDEL POST NEWS
ዘ ቴሌግራፍ ያወጣው አዲስ የድምፅ ቅጂ፤ ሞጅታባ ኻሜኒ እንዴት ተረፉ?
​
​ብሪታንያዊው ጋዜጣ ዘ ቴሌግራፍ ባወጣው አዲስ መረጃ፣ አዲሱ የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በቴህራን በተፈጸመው መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ለጥቂት መትረፋቸውን ይፋ አደረገ።

ጋዜጣው እጄ ገብቶኛል ባለው የድምፅ ቅጂ መሠረት፣ ሞጅታባ ኻሜኒ ከሞት የተረፉት በወቅቱ በነበረ "አጋጣሚ" መሆኑ ታውቋል።
​
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው የካቲት 21 ቀን ረፋድ 3:32 ላይ ሲሆን፣ በአሜሪካና በእስራኤል የተወነጨፉ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች የመሪውን መኖሪያ ግቢ በከፍተኛ ሁኔታ ደብድበዋል።

በወቅቱ የጽሕፈት ቤቱ የፕሮቶኮል ኃላፊ የነበሩት ማዛሄር ሆሴይኒ በድምፅ ቅጂው ላይ እንደገለጹት፣ ሞጅታባ ኻሜኒ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ "አንድ ጉዳይ ለመፈጸም" ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ወጥተው ነበር።

ይህ አጋጣሚ ሕይወታቸው እንዲተርፍ አድርጓል።
​
ምንም እንኳን ሞጅታባ ኻሜኒ በእግራቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ቢተርፉም፣ ጥቃቱ በቤተሰባቸው ላይ ግን የከፋ ነበር።

ጥቃቱ ሙሉውን የኢራን አመራርና የኻሜኒን ቤተሰብ ለማጥፋት ታቅዶ የተፈጸመ መሆኑን ሆሴይኒ ገልጸዋል።

ሞጅታባ ኻሜኒ ጥቃቱን ቢተርፉም፣ እስካሁን በሕዝብ ፊት አለመታየታቸውና መልእክቶቻቸው በጽሑፍ ብቻ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን መተላለፋቸው ስለ ጤንነታቸው ሁኔታ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.