Logo
FIDEL POST NEWS
አርሰናል ከሜዳው ውጭ ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር አቻ ተለያየ

​በሻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ አርሰናል ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ የሌቨርኩሰኑ አምበል ሮበርት አንድሪች በግንባር በመግጨት ቡድኑን መሪ ቢያደርግም፣ መድፈኞቹ እስከ ጨዋታው መጠናቀቂያ ድረስ ሲታገሉ ቆይተዋል።

​በ89ኛው ደቂቃ ላይ ኖኒ ማዱዌኬ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ ተጠልፎ በመውደቁ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ካይ ሀቨርትዝ ተረጋግቶ በምታት ከመረብ አሳርፎታል።

ቀደም ብሎ ጋብሪኤል ማርቲኔሊ የመታው ኳስ በግቡ አግዳሚ የተመለሰ ሲሆን፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያም አስገራሚ ኳሶችን አድኗል።

ውጤቱ ለአርሰናል ለቀጣዩ ሳምንት በሜዳው ለሚያደርግ ጨዋታ መልካም አጋጣሚን የፈጠረ ሆኗል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.