የዓለማችን ቁጥር አንድ የዕፅ አባት በዱባይ ታየ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈለገውና "ዳፐር ዶን" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው አይሪሻዊው የዕፅ አዘዋዋሪ ክሪስቲ ኪናሃን፣ ከዓመታት መደበቅ በኋላ በዱባይ መታየቱ ተሰምቷል።
የ69 ዓመቱ ኪናሃን ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ ከልጁ ዳንኤል ኪናሃን ጋር በዱባይ በሚገኝ የስፖርት መድረክ የቪአይፒ ወንበር ላይ ተቀምጦ ተስተውሏል።
የኪናሃን ካርቴል በአውሮፓ የኮኬይን ዝውውር፣ በገንዘብ ማጠብና በዓለም አቀፍ የተደራጁ ወንጀሎች ላይ እጁ እንዳለበት ይታመናል።
አሜሪካ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ የ5 ሚሊዮን ዶላር የሹልማት ገንዘብ መመደቧ የሚታወስ ሲሆን፣ የካርቴሉ ሀብትም 1.5 ቢሊዮን ፓውንድ እንደሚደርስ ይገመታል።
ምንም እንኳን ግለሰቡ ማንነቱን ለመደበቅ ልዩ ስልጠናዎችን ቢወስድም፣ በቅርቡ በታየበት ወቅት ግን ራሱን ለመደበቅ ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጉ ብዙዎችን አስገርሟል።
ምንጭ፦ Newspaper Article

7 months ago