Logo
Getu Temesgen
''ለቤተ መቅደሱ ግንባታ እንተጋለን ''

የፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለአዲሱ ሕንጻ ግንባታ ማጠናቀቂያ የሚውል 70 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታላቅ ዓለም አቀፍ የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

በሰሜን አዲስ አበባ ተራራማ ስፍራ ላይ የሚገኘውና ከአዲስ አበባ ዙሪያ በማንኛውም አቅጣጫ ሊታይ የሚችለው ይህ ደብር፣ ከነሐሴ 23 ቀን 1983 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም፣ እየጨመረ የመጣውን የምዕመናን ቁጥር ታሳቢ በማድረግና አገልግሎቱን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለማስፋፋት አዲስ የሕንጻ ግንባታ በ2008 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።

ባለፉት 10 ዓመታት በደብሩ አገልጋዮችና በምዕመናን ብርቱ ጥረት የሕንጻው መዋቅር (ስትራክቸር) ሥራ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ አሁን ላይ የሕንጻው ግንባታ ከመሬት በላይ 48 ሜትር ርዝመት ደርሶ ወደ ማጠናቀቂያ ወይም የፊኒሺንግ ስራዎች ተሸጋግሯል።

እንደ ጋዜጣዊ መግለጫው ማብራሪያ፣ በአሁኑ ወቅት የውስጥ ግድግዳና የጂፕሰም ሥራዎች፣ የቅዱሳን ሥዕላት፣ የግድግዳ የእንጨት ክላዲንግ፣ የመሬት ወለል የግራናይት ንጣፍ እንዲሁም የኤሌክትሪክና የድምፅ ሲስተም ዝርጋታዎች የሚቀሩ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው።

እነዚህን ሥራዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግም “ለቤተ መቅደሱ ግንባታ እንተጋለን” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 20 እስከ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል።

ይህ መርሐ ግብር በየቀኑ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት ድረስ በቤተክርስቲያኑ የዩቱዩብ፣ የቲክቶክ፣ የፌስቡክና የቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በተለያዩ ሚዲያዎች በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆችና ምዕመናን በስልክ ጥሪና በባንክ አካውንቶች ድጋፋቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻም ይህ የቤተክርስቲያን ግንባታ ለትውልድ የሚተላለፍ መንፈሳዊ ሀብት በመሆኑ፣ ሁሉም ምዕመናን አሻራቸውን እንዲያሳርፉና በታሪክ ውስጥ ስማቸውን እንዲያስመዘግቡ የተጠየቀ ሲሆን፣ በመርሐ ግብሩ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ለሚያደርጉ ምዕመናን የክርስትና ስማቸው በክብር መዝገብ ላይ ተመዝግቦ በጸሎት እንደሚታሰቡም የደብሩ ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

በመሆኑም በመላው ዓለም የሚገኙ ምዕመናን ለመደገፍ እና ለመሳተፍ የሚከተሉትን የባንክ አካውንቶች እንዲጠቀሙ ተጠይቋል

🔹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000071660487 በአጭር ቁጥር: 2319 swift code - CBETETAA
🔹 አቢሲኒያ ባንክ: 251260001swift cde -ABYSETAA
🔹 አዋሽ ባንክ: 013521736087000 swift code -AWINETAA
🔹 ዳሸን ባንክ: 5253970507011 swift code - DASHETAA
🔹 አባይ ባንክ: 1521112863200018 swift code - ABAYETAA
🔹 አሀዱ ባንክ: 0089051320301 swift code - AHUUETAA

🌐 በወገን ፈንድ (Wegenfund): ሊንኩን ይጫኑhttps://www.wegenfund.com/...

📞 በቴሌ ብር
0993761212 / 0992641212 / 0993321212 ድጋፋቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።

በመግለጫው ላይ የተገኙት የደብሩ የሰበካ ጉባኤ እና የኮሚቴ አባላት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆች ግንባታው ለፍጻሜው እንዲደርስ በገንዘባቸውና በዕውቀታቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.