የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ በአዲስ አበባ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ውይይቱ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብርን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የታሪክና የባህል ትስስር ጠንካራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም የቤተ-እስራኤል ማህበረሰብ በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደ ህያው ድልድይ እንደሚያገለግሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ያለውን ግጭት በተመለከተ፣ ሁለቱ ሀገራት በሰላም ጎን ለጎን የሚኖሩበትን የ"ሁለት ሀገራት" (Two-state solution) መፍትሄ በጽኑ እንደምትደግፍ ሚኒስትሩ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ በቆይታቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ አሻራ እና የነጻነት ተምሳሌትነት አድንቀዋል።

8 months ago