በአማራ ክልል በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚደርስ ድብደባና ግድያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እንዳሳሰባቸው የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናገሩ፡፡
ጉዳዩም በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ጠይቀዋል፡፡
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰራጩት መረጃ በአማራ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የጤና ባለሙያዎችን ያነጣጠረ የመታሰር ፣ የመደብደብ የግድያ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለአብነትም የካቲት 4 ቀን የሕክምና ባለሙያው ዶ/ር ፀጋሁን ስሜ በባህር ዳር ተገድሎ መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡
በግጭቱም ሆስፒታሎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ፣ የእርዳታ ሰራተኞችም ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ ባወጡት መረጃ ይፋ አድርገዋል፡፡
የጤና ተቋማትና የጤና ባለሙያዎች የጥቃት ዒላማ መሆን የለባቸውም ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በገለልተኛ አካል ለጥፋቱ ተጠያቂዎች የሆኑት እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡
Sheger Fm

8 months ago