ኢትዮጵያ በዓመት 300 ሚሊዮን ኮንዶም እንደሚያስፈልጋት ተነገረ
👉 በዛሬው እለት ዓለም አቀፉ የኮንዶም ቀን እየተከበረ ይገኛል
ዓለም አቀፍ የኮንዶም ቀን በዛሬው ዕለት እየተከበረ ሲሆን ሶስት ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከበር መሆኑ ተገልጿል ። ይህም ያልተፈለገ እርግዝና ፣ኤችአይቪ እና የአባላዘር በሽታ መከላከል እና በትክክል ኮንዶምን መጠቀም እና አቅርቦትን ያካትታል።
በየጊዜው ኮንዶሞችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያቀርበው ኤድሰ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን አሁንም በኢትዮጲያ ወስጥ የኮንዶም አቅርቦት እጥረት መኖሩን ከብስራት ሬዲዮና ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤድሰ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን የኤች አይ ቪ መከላከል የአፍላ ህይወት ላይዘንና አድቮኬሲ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቶሎሳ ኦላና ገልጸዋል።
በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ኮንዶም ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት በነፃ እያከፋፈለ እንደሚገኝ በመግለጽ በቅርብ ደግሞ ከውጪ ወደ 6 ሚሊዮን ኮንዶም ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚደረግ አንስተዋል። ይሁን እና አሁንም በኢትዮጵያ ያለው የኮንዶም አቅርቦት ከፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ኤች አይቪ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል እስከ ከ300 ሚሊዮን በላይ ኮንዶም ያስፈልጋታል ተብሏል።
ነገር ግን ኤኤችኤፍም ሆነ ሌሎች በተመሳሳይ ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች የሚያስገቡት የኮንዶም ቁጥር ተደምሮ የሀገሪቱን የኮንዶም ፍላጎት ሊሟላ ያልተቻለበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ስራ ከውጭ ሀገራት በሚገኝ ድጋፍ ለረዥም ጊዜ ሲሰራበት የቆየ ነው። ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ኮንዶም በበቂ ሁኔታ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እየተሰራ ሲሆን ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የሚቻልበት አሰራር በመፈጠሩ የተሻለ ለመስራት እድል እንደሚከፍት አቶ ቶሎሳ ኦላና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

8 months ago