ከመጠን ያለፈ የሰውነት ውፍረት ለሞት ለሚያደርሱ ኢንፌክሽኖች የመጋለጥ እድልን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ተገለጸ::
ከመጠን ያለፈ የሰውነት ውፍረት ከ10 በመቶ በላይ ለሚሆኑ ከኢንፌክሽን ጋር ለተያያዙ የሞት አደጋዎች መንስኤ ሊሆን እንደሚችል አንድ አዲስ ጥናት ይፋ አድርጓል።
በታዋቂው የሕክምና መጽሔት ላንሴት ላይ የታተመው ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት መመጠኛ(BMI) ያላቸው ሰዎች ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ነው።
ተመራማሪዎቹ በፊንላንድ እና በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ አዋቂዎችን የጤና መረጃ ለ14 ዓመታት ያህል የተነተኑ ሲሆን፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች በኢንፌክሽን ምክንያት ለሞት ወይም ለከባድ ሕመም የመጋለጥ እድላቸው ከጤናማ ሰዎች በ70 በመቶ እንደሚበልጥ አረጋግጠዋል።
በተለይም የሰውነት ክብደት መመጠኛቸው 40 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ወይንም በደረጃ 3 ውፍረት ውስጥ የሚመደቡ ሰዎች በበሽታው የመጠቃት እድላቸው በሦስት እጥፍ የጨመረ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ የጤና ስጋት አሳሳቢ የሚሆነው ደግሞ ችግሩ የታየው ከመጠን ያለፈ ውፍረት ባለባቸው ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ስኳር እና የልብ ሕመም ያሉ ተጓዳኝ የጤና እክሎች በሌለባቸው ሰዎች ላይም ጭምር መሆኑ ነው።
ጥናቱ እንደ ኮቪድ-19፣ የሳንባ ምች፣ የሽንት ቧንቧ እና የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖችን ጨምሮ ከ900 በላይ የባክቴሪያ፣ የቫይረስ እና የፈንገስ በሽታዎችን የመረመረ ሲሆን፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንኳን ይህንን ከመጠን ያለፈ ውፍረትና ከኢንፌክሽን ስጋት ጋር ያለውን ቁርኝት ሊያስቀረው አለመቻሉ ተመልክቷል።
ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ስሌት መሠረት፣ በፈረንጆቹ 2021 ከተመዘገቡት የኢንፌክሽን ሞቶች ውስጥ እስከ 15 በመቶ የሚሆኑት ከሰውነት ውፍረት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ነበራቸው።
ይህም የሰውነት ክብደትን በአግባቡ መቆጣጠር ከተላላፊ በሽታዎች ራስን ለመጠበቅና የመከላከል አቅምን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን እንደሚያሳይ ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
seledadotio

8 months ago