Logo
FIDEL POST NEWS
የትዳር አጋርዎ እየከዳዎት መሆኑን በ30 ሰከንድ ውስጥ እንዴት ማወቅ ይቻላል? የግል መርማሪው ሚስጥር

​በትዳር ወይም በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ጥርጣሬ ሲገባ ሰላም ማጣት የታወቀ ነው። የትዳር አጋርዎ ስልኩን ደብቆ መያዝ፣ ስልኩን በግልባጭ ማስቀመጥ ወይም ሚስጥራዊ መሆን ከጀመረ "ሌላ ሰው ይኖር ይሆን?" ብሎ መጠርጠር ተፈጥሯዊ ነው።

​ታዋቂው የግል መርማሪ ፖል ኢቫንስ (Paul Evans)፣ የግንኙነት ታማኝነትን ለመፈተሽ የሚያስችል እጅግ ቀላል እና ፈጣን ዘዴን ይፋ አድርጓል።

​የቴክኖሎጂው ዘመን እና ክህደት

​ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአሁኑ ወቅት ሰዎች ለክህደት በብዛት የሚጠቀሙት የኢንተርኔት አማራጮችን ነው።

Cyberpsychology, Behavior, and Social Networking የተባለው መጽሔት ባወጣው ጥናት መሠረት፣ በዴቲንግ (Dating) መተግበሪያዎች ላይ ከሚገኙ ተጠቃሚዎች መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት በትዳር ውስጥ ወይም በቁርጥ ያለ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ናቸው።

​መርማሪው የሚመክሩት የ30 ሰከንድ ዘዴ
​እንደ ቲንደር (Tinder) ያሉ መተግበሪያዎች ለጊዜያዊ ግንኙነት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ፖል ኢቫንስ እንደሚለው፣ የትዳር አጋርዎ እነዚህን መተግበሪያዎች እየተጠቀመ መሆኑን ለማወቅ የእሱን ስልክ መንካት ወይም የውስጥ መልዕክቱን ማንበብ አያስፈልግዎትም።

​መንገዱም የሚከተለው ነው፦

👉​ወደ ታዋቂ የዴቲንግ ድህረ-ገጾች ወይም መተግበሪያዎች ይሂዱ።
👉​በአዲስ ተጠቃሚነት ለመመዝገብ ይሞክሩ።
​ለመመዝገቢያነት የትዳር አጋርዎን የኢሜይል አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ያስገቡ።

​"ይህን ሲያደርጉ ሲስተሙ ወይ አካውንት እንዲከፍቱ ይፈቅድልዎታል (ይህ ማለት አድራሻው አልተመዘገበም ማለት ነው)፣ ወይም ደግሞ 'ይህ ኢሜይል ቀድሞ ተይዟል' (Email already in use) የሚል መልዕክት ያሳየዎታል።" ይላል መርማሪ ኢቫንስ።

​ይህ መልዕክት ከመጣ፣ ያ የኢሜይል አድራሻ በዚያ ድህረ-ገጽ ላይ አካውንት ለመክፈት ጥቅም ላይ መዋሉን የሚያረጋግጥ ፍንጭ ነው።

​ጥንቃቄ ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦች

​ይህ ዘዴ አካውንት መኖሩን ቢያረጋግጥም፣ ወዲያውኑ "እየከዳኝ/ችኝ ነው" ወደሚል ድምዳሜ ላይ ላይያደርስ ይችላል።

ፖል ኢቫንስ የሚከተሉትን ነጥቦች ያስገነዝባል፦

​የቆየ አካውንት፦ አካውንቱ ግንኙነታችሁ ከመጀመሩ በፊት የተከፈተ ሊሆን ይችላል።

​የግንኙነቱ ርዝመት፦ "ለበርካታ ዓመታት አብራችሁ ከቆያችሁ እና አድራሻው አሁንም በስራ ላይ ከሆነ ግን ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው" ይላል መርማሪው።

​ለእርስዎ፦ ይህንን መረጃ በመጠቀም የትዳር አጋርዎ የዴቲንግ መተግበሪያ ላይ መኖሩን ማረጋገጥ ቢችሉም፣ ዋናው መፍትሄ ግልጽ ውይይት እንደሆነ አይዘንጉ።
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.