Logo
FIDEL POST NEWS
አሜሪካ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) መታ ጣለች

አንደ ሬውተርስ ዘገባ ​በአረቢያ ባህር ላይ ሲጓዝ በነበረው USS Abraham Lincoln በተሰኘው የአሜሪካ የጥቃት አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ ሊቃረብ የነበረ የኢራን ድሮን መመታቱ ተገለጸ።

​ምን ተከሰተ? "ሻሄድ-139" የተሰኘችው የኢራን ድሮን ወደ አሜሪካ የጦር መርከብ በከፍተኛ ፍጥነት ስትቃረብ፣ በአሜሪካው F-35 ተዋጊ ጄት ተመትታ ወድቃለች።

​ቦታው፦ ክስተቱ የተፈጠረው ከአረቢያ ባህር ላይ፣ ከኢራን ደቡባዊ የባህር ጠረፍ በግምት 800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው።

​ምክንያት፦ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ቃል አቀባይ ካፒቴን ቲም ሃውኪንስ እንደገለጹት፤ ድሮኗ መርከቧን "በጥቃት መንፈስ" ስለተቃረበች ለራስ መከላከያ ሲባል ተመትታለች።

​ጉዳት፦ በዚህ እርምጃ ምንም አይነት የአሜሪካ ወታደርም ሆነ ንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም።

​ተጨማሪ ውጥረት፦
በተመሳሳይ ቀን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ጀልባዎች የአሜሪካ ሰንደቅ አላማ የጫነን የንግድ መርከብ ለመጥለፍ ሙከራ ማድረጋቸው ተነግሯል። አሜሪካ ይህን መሰል "ትንኮሳዎችን አንታገስም" ስትል አስጠንቅቃለች።
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.