"ብፁዕ ዘይሁብ እምዘይነሥእ፤ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" (ሐዋ. ፳÷፴፭)
#ethiopia | የካራ ወሰዋ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በድምቀት ተመረቀ
• ለቤተክርስቲያኒቱ ግንባታ ማጠናቀቂያ በሊቀ ብርሃናት ዲያቆን ምትኩ ልዑል ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።
• ለቤተክርስቲያኑ የውስጥ ምንጣፍና መቀመጫ ወንበሮች በአቶ ዮሐንስ ከ500 ሺህ ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።
(ሉሜ፣ ምሥራቅ ሸዋ) በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ወረዳ የሚገኘውና ለሰባት ዓመታት በግንባታ ላይ የቆየው የካራ ወሰዋ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን፣ ሰሞኑን የቅዳሴ ቤቱ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል።
የመሠረት ድንጋይና የአባቶች ራዕይ
ታሪኩ የሚጀምረው መምሬ አርጋው መንግስቱ እና ቀሲስ ኃይለሚካኤል መንግስቱ በተባሉ አርቆ አሳቢ ወንድማማች ካህናት ጥረት ነው። እኚህ አባቶች የአካባቢውን አባወራዎች ሰብስበው፦ "እስከ መቼ የካራ ወሰዋ ምእመናን ለክርስትና እና ለሥርዓተ ቀብር ወደ ሩቅ ቦታ እንጓዛለን? እስከ መቼስ አስክሬናችንን አርቀን በመውሰድ እንሳቀያለን? ለዚህ መልስ አምጡ!" ሲሉ በቁጭት ጠየቁ።
ከዚህ ታላቅ ጥሪ በኋላ፣ ከተሰበሰቡት 68 አባወራዎች መካከል አንድ አባት እጃቸውን አወጡ። በቦታው የነበረው ምእመን በጉጉት ሲጠባበቅ እኚህ አባት፦ "ለሥጋ ወደሙና ለክርስትና ሩቅ መሄዳችን አሰልችቶናል። በአጥቢያው ቤተክርስቲያን ባለመኖሩም ፊታቸውን የሚያጠቁሩብን አልጠፉም። ስለሆነም ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ የመሬቴን ሲሶ (ሩብ) እሰጣለሁ" አሉ። በወቅቱ ጭብጨባው ደመቀ፤ ምርቃቱም ከየአቅጣጫው ጎረፈ። የዚህ ደግ አባት ተግባር ሌሎች ሦስት አባወራዎችን አነሳስቶ እነርሱም የመሬታቸውን ሲሶ ሰጡ።
ይሁን እንጂ ደስታው ብዙ አልቆየም። ቦታው ለቤተክርስቲያን ግንባታ አመቺ አይደለም መባሉ ትካዜን ፈጠረ። ይህንን የተረዱት አቶ ጥላሁን ያደና "ለእግዚአብሔር ቤት ያልሆነ መሬት ለምን ሊሆን ነው? እኔስ የክርስቶስ አይደለሁም ወይ?" በማለት ለግንባታው አመቺ የሆነውን ቦታ በለውጥ ሰጡ። በዚህም መሠረት የቃል ኪዳኑ ታቦት ከዝዋይ ሐመረ ኖህ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መጥቶ በ2011 ዓ.ም በመቃኞ፣ ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ የአሁኑ ሰፊ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
አደራን የመጠበቅ ጽናት
የቤተክርስቲያኑ ግንባታ እንዲሳለጥ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩትና አቃቂ ከተማ የሚኖሩት ነፍሰ-ኄር ወልደ ጊዮርጊስ (ቸሬ)፣ ሕልማቸው ሳይፈጸም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሆኖም ወዳጆቻቸው "የወንድማችን አደራ ዕዳ ይሆንብናል" በማለት ግንባታውን ቀጠሉበት።
ይህ የአደራ ጥሪ በመጨረሻ ለሊቀ ብርሃናት ዲያቆን ምትኩ ልዑል ደረሰ። ዲያቆን ምትኩ ላለፉት አምስት ዓመታት ግንባታውን ሲደግፉ ቆይተው፣ በተለይ ባለፉት ሁለት ወራት የተከናወነውን የፊኒሺንግ ሥራ ጨምሮ በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ቤተክርስቲያኑ ለምረቃ እንዲበቃ አድርገዋል። ይህ ተግባራቸውም "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" (ሐዋ. ፳÷፴፭) የሚለውን ቃል በተግባር የገለጸ ሆኗል።
በተያያዘም አቶ ዮሐንስ የተባሉ በጎ አድራጊ ከ500 ሺህ ብር በላይ በማውጣት ለቤተክርስቲያኑ ምቹ ምንጣፍና የመቀመጫ ወንበሮችን አበርክተዋል። ለቤተክርስቲያኑ ግንባታ በርካታ ምዕመናን የየራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ሲሆን፣ አምላከ ቅዱስ ገብርኤል በረድኤቱ እንዲጎበኛቸው ተመኝተዋል።
ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ መሳካት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከማሰባሰቡ ባሻገር፣ የግንባታውን ሥራ በቅርበት በመከታተልና በማስተባበር ረገድ የአቶ ሲሳይ ንጉሴ ሚና እጅግ የላቀ ነበር። አቶ ሲሳይ ለህንጻ ቤተክርስቲያኑ ፍጻሜ ሲል ላለፉት ሁለት ወራት ቤቱን፣ ባለቤቱንና ልጆቹን በመተው፤ የግል ምቾቱን መሥዋዕት አድርጎ በሥፍራው አድሮና ውሎ ሥራውን በትጋት ሲመራ ቆይቷል። ይህ በቤተክርስቲያን ታሪክ 'እንደ ባለ አደራ' የታየው ታላቅ የክርስቲያናዊ ኃላፊነት መወጣት፣ ለቤተክርስቲያኑ በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ እንደ ዋነኛ ምሰሶ ተጠቃሽ ሆኗል።
ደማቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓትና የቀጣይ ዕቅድ
በምረቃው ዕለት ከአቃቂ መንበረ ሕይወት፣ ከቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም፣ ከጃቴ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ከመጋላ ደብረ ምህረት ቅዱስ አማኑኤል የተገኙ ሊቃውንትና የሰንበት ተማሪዎች በዝማሬና በማኅሌት ቅዳሴ ቤቱን አድምቀውታል።
ቀጣይ ዕቅድ
በቀጣይም ተተኪ አገልጋዮችን የሚያፈራ የአብነት ትምህርት ቤት ለመገንባትና ቤተክርስቲያኑ ራሱን የቻለ ገቢ እንዲኖረው የወፍጮ ቤት ግንባታ ለማከናወን ታቅዷል። በበዓሉ ማጠቃለያ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከከተማ ለመጡ እንግዶች ያላቸውን አክብሮት በሀገር ባህል ምርቃትና በእንባ በተናነቀ ምስጋና ገልጸው በታላቅ ፍቅር ሸኝተዋቸዋል።

8 months ago