ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ በኩል የባህር በር ፍላጎቷን ለማሳካት የኃያላን ሀገራትን ድጋፍ ማስተባበር እንዳለባት ተገለጸ
ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ በኩል የባህር በር ፍላጎቷን ለማሳካት እንደ እስራኤል ሁሉ የሌሎች ኃያላን ሀገራትን እውቅና ማስተባበር እንዳለባት ተገለጸ። የሶማሌላንድ ሀገርነት በይፋ የተረጋገጠ ስላልሆነ ኢትዮጵያ ስልታዊ አካሄድ መከተል እንዳለባት የገለጹት የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው ዶክተር ጌትዬ ትርፌ፤ ሀገሪቱ በቀጠናው ያላትን ተቀባይነት ተጠቅማ እንደ እስራኤል ሁሉ ሌሎች ኃያላን ሀገራት እውቅና እንዲሰጡና የሁለቱ ሀገራት ጥቅም እንዲከበር ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሶማሌላንድ ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ የምትሰጥ መሆኗን የገለጹት ባለሙያው፤ የተለያዩ ሀገራት በተናጠል የሀገርነት እውቅና እየሰጧት ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ስልታዊ በማድረግ እውቅና የሚሰጡ ሀገራትም ተመሳሳይ ፍላጎት ሊኖራቸው ስለሚችል ጉዳዩን በብስለት ማጤን እንደሚገባት አመላክተዋል። በተለይም የእስራኤልን እውቅና መስጠት እና የአሜሪካን ዝምታ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በሶማሌላንድ በኩል የባህር በር ማግኘት የሚቻልበትን አማራጭ ማጤን ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ስልታዊ የሆነ አካሄድን እየተከተለች ነው ብዬ አምናለሁ ያሉት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪው ዶክተር አብዱ ሞሐመድ ናቸው። የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት በዳቮሱ ስብሰባ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የባህር በር ለመስጠት አዎንታዊ ምላሽ እንዳላት ያስተላለፉትን መልዕክት ኢትዮጵያ ልታጤነው እንደሚገባ ገልጸዋል።
እስራኤል ለሶማሌላንድ እውቅና ስለሰጠች በኢትዮጵያ መንግስት በኩል መረጋጋት መታየቱ ለቀጠናው መልካም የሚባል አካሄድ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የእስራኤልን ፈለግ እንዲከተሉ የጠነከረ ዲፕሎማሲያዊ የማግባባት ስራ ከኢትዮጵያ እንደሚጠበቅ አክለዋል። ምንም እንኳን ከሶማሌላንድ በኩል አዎንታዊ ምላሽ ቢኖርም፣ ኢትዮጵያ የተረጋጋ አካሄድን መከተሏ በቀጠናው ያላትን ተቀባይነት የበለጠ ለማሳደግ እንደሚረዳ አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑንና ሀገሪቱ በቀጠናው ሰላምና ደህንነት ላይ የሚጠበቅባትን ሚና እንድትጫወት የተሻለ ዕድል እንደሚፈጥርም ባለሙያዎቹ አስገንዝበዋል።
seledadotio

8 months ago