የንግድ ማህበራት አይነት
አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ አዋጅ ቁጥር 1243/13
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037,0983337690
መግቢያ #ethiopia | ሰዎች በኢኮኖሚያዊ እንቀስቃሴ ለመሰማራት በህብረት ገንዘብ እውቀት ሙያ ንብረት ጉልበታቸውን በማወጣት ተደራጅተው ከሚገኘዉ ትርፍ ተካፋይ ለመሆን በመመስረቻ ጽሁፍ አማካኝነት ህጋዊ የንግድ ማህበር ያቋቁማሉ።የንግድ ማህበራት አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ዕውቀታቸውን፣ በዚህ አጭር ጽሁፍ አጠቃላይ የንግድ ማህበራትን በህጉ የተካተቱን በመጥቀስ በተለይም የባለ አንድ አባል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን በተመለከት በተለየ መልኩ በማንሳት ግንዛቤን ለማስጨበጥ እንሞክራለን።
1. የንግድ መኅበራት ጽንሰ ሀሳብ በኢፊድሪ ህገመንግስት...
ሰወች በግልም በሆነ በህብረት የንግድ ስራን የመስራት መብት በኢፊድሪ ህገ መንግስት በቀድሞውም ሆነ በአዲሱ የንግድ አዋጅ ሆነ በሌሎች አግባብነት ያላቸው አዋጆች የተሰጠ መብት ነው። የንግድ ስራዎችን ለመስራት የመደራጀት መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 31 ላይ “ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው፡፡ ይህም በንግድ ማህበር የመደራጀትን መብት የሚፈቅድ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ ይህ በንግድ ማህበራት የመደራጀት መብት በህገመንግስቱ አንቀፅ 41(2) “ሁሉም ኢትዮጵያዊ መተዳደርያውን ስራውንና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው” ከሚለው ህገ-መንግስታዊ መብት አንፃር ያየነው እንደሆነም ዜጎች አዋጪ ነው ባሉት የንግድ ማህበር መርጠው እንደመተዳደርያ ስራቸው አድርው መውሰድ ይችላሉ።
2. የንግድ ማህበራት አይነቶች በአዲሱ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/13
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 174 መሰረት በእኛ ሀገር ሰባት ዓይነት የንግድ ማኅበራት አሉ፡፡ እነሱም፡-
የኅብረት ሽርክና ማኅበር / General Partnership/
ሁለት አይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማህበር /Limited Partnership/
ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር /Limited Liability Partnership/
የአሽሙር ማህበር /Joint Ventur/
የአክሲዮን ማህበር /Share Company/
ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር /Private Limited Company/ እና
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር / One Person private limited Company/ ናቸው፡፡
2.1. የኅብረት ሽርክና ማህበር
የህብረት ሽርክና ማህበር በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 283 መሰረት ማኅበርተኞች እያንዳንዳቸው ባንድነትና ሳይከፋፈል እርስ በርሳቸውና ለማህበሩ ግዴታዎች አላፊዎች የሚሆኑበት ማኅበር ነው፡፡ ይህም ማለት ማህበሩ ለሚያጋጥመው አደጋ ወይም እዳ ሁሉ እያንዳንዱ አባል በግሉ፣ ወይም ሁሉም በአንድነት ወይም ከሁሉም የተወሰኑት ብቻ በተናጥል ለእዳው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ማንኛዉም ተቃራኒ ስምምነት ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ሊሆን አይችልም፡፡
2.2. ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማኅበር....
ሁለት ዓይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማኅበር ከስሙ እንደምንረዳው የማኅበርተኞቹ ኃላፊነት የተለያየ የሆነበት ማኅበር ነዉ፡፡ እነሱም ኃላፊነታቸዉ ያልተወሰነ ሸሪኮችና ኃላፊነታቸዉ የተወሰነ ሸሪኮች ናቸው፡፡ በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 212 መሰረት ኃላፊነታቸው ያልተወሰነ ሸሪኮች የሚባሉት ለማኅበሩ ግዴታዎች በሙሉ ከማኅበሩ ጋር በአንድነትና በተናጠል ኃላፊነት ያለባቸዉ ሲሆን ኃላፊነታቸዉ የተወሰነ ሸሪኮች ደግሞ መዋጮ ለማድረግ ቃል በገቡት መጠን ብቻ ለማኅበሩ ግዴታች ኃላፊ የሚሆኑ ናቸዉ፡፡ ኃላፊነታቸው የተወሰነ ሸሪኮች በወክልናም ሆነ በሌላ በማንኛዉም ሁኔታ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆን አይችሉም፡፡
2.3.ኃላፊነታቸው የተወሰነ የሙያ ሽርክና ማኅበራት ....
በአዲሱ የንግድ ህግ ውስጥ ከተካተቱ ጉልህ ለውጦች መካከል አንዱ የሆነው ይህ አዲስ የሽርክና ማህበር አይነት፣ ሰዎች በተለይም የሙያ ስራዎችን ለመስራት በሙያ ከሚመስሏቸው ሌሎች ሰዎችና ለሙያው ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ሊሰጡ ከሚችሉ አጋሮቻቸው ጋር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው የሚያቋቁሙት እና ኃላፊነቱም በሽርክና ማኅበሩ ሃብት ላይ ብቻ የተወሰነ የንግድ ማኅበር ነው።
2.4 የአሽሙር ማህበር....
የአሽሙር ማህበር ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች በመካከላቸዉ በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚያቋቁሙት ሲሆን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው በጽሁፍ መረጋገጥና በሌሎች የንግድ ማህበሮች የተደነገጉ የማስመዝገብ ሰርዓቶች የማይፈፀሙበት፣ የሕግ ሰዉነት የሌለውና በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ የማይታወቅ መሆኑ ሲሆን ከታወቀ ግን እንደ ሕብረት ሽርክና ማህበር እንደሚቆጠር ሊታወቅ ይገባል፡፡
2.5 የአክሲዮን ማህበር...
የአክሲዮን ማህበር ማለት በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 245 መሰረት ዋናው ገንዘቡ ወይም ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክስዮን የተከፋፈለና ኃላፊነቱ በማኅበሩ ሀብት ብቻ የተወሰነ (ለዕዳው ንብረቱ ብቻ ዋስ የሆነ) ማኅበር ነው፡፡
2.6 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር...
በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 495 መሰረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማለት ዋና ገንዘቡ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ፣ በአክስዮን የተከፈለ እና ባለአክስዮኖች መዋጮቸዉን ገቢ እስካደረጉ ድረስ ለማኅበሩ ዕዳ ኃላፊ የማይሆኑበት የንግድ ማኅበር ነዉ፡፡
2.7 ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ...
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማለት አንድ ሰዉ በግሉ በሚሰጠዉ መግለጫ መሰረት የተቋቋመ የንግድ ማኅበር ነዉ፡፡ ማኅበሩ ከአባሉ የተለየና የተነጠለ የራሱ የሕግ ሰዉነት አለዉ፡፡ አባሉ የራሱን መወጮ ሙሉ በሙሉ እስከ ከፈለ ድረስ ማኅበሩ ላይ ለሚፈለገዉ ዕዳ በግሉ አይጠየቅም፡፡ የማኅበሩ ዝቅተኛ ዋና ገንዘብ ከ ብር አስራ አምስት ሺህ ማነስ የለበትም፡፡ ማኅበሩን ለማቋቋም አባሉ የሚሰጠዉ መግለጫ ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት መደረግ አለበት፡፡ መግለጫዉም በንግድ መዝገብ ዉስጥ መግባት አለበት፡፡ ግለሰብ ነጋዴ የንግድ ሥራዉን ወደ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርነት መለወጥ ይችላል፡፡ ይቻላል።
3.1 የህግ ምክር
በአዲስ የንግድ ህጋችን ላይ የተቀመጡትን የንግድ ማህበራት በተገቢው መንገድ በመረዳት ነጋዴው ያሻውን በመምረጥ መስራት የሚችል ሲሆን ሌላይኛውም ማህበረሰብ ፣ ባለሙያዎች ቀድሞ ግንዛቤ መውሰድ አስፈላጊ ነው።
https://www.facebook.com
https://t.me/Fantahunlawye...

6 months ago