Logo
FIDEL POST NEWS
፡ "እኔ የባዕድ ፍጡር (Alien) ነኝ!" — ኢሎን ማስክ

​በዳቮስ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም (WEF 2026) ላይ ያልተጠበቀ ንግግር ያደረገው ቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ፣ ከብላክሮክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ላሪ ፊንክ ጋር በነበረው ቆይታ አስገራሚ ቀልዶችን አጋርቷል።

​ስለ ባዕድ ፍጡራን፦ ማስክ "ሰዎች ሁልጊዜ 'መካከላችን Alien አለ ወይ?' ብለው ይጠይቁኛል። እኔም 'አዎ እኔ ራሴ አንዱ ነኝ' እላቸዋለሁ፤ ግን ማንም አያምነኝም" በማለት በፈገግታ ተናግሯል።

​ማስረጃው፦ ስፔስ ኤክስ (SpaceX) እስካሁን ከ9,000 በላይ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ቢልኩም፣ አንድም የባዕድ ፍጡራን መንኮራኩር አጋጥሟቸው እንደማያውቅና ይህም በህዋ ላይ ህይወት ምን ያህል ብርቅ እንደሆነ እንደሚያሳይ ገልጿል።

​የወደፊት ትንበያ፦ በ2026 ማብቂያ ላይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ከሰው ልጅ ብልህነት በላይ እንደሚሆንና በቅርቡም የሮቦቶች ቁጥር ከሰው ልጆች እንደሚበልጥ ትንቢቱን ተናግሯል።

​ማስክ አክሎም "በመካከላችን Alien ቢኖር ኖሮ መጀመሪያ የማውቀው እኔ ነበርኩ" በማለት ተደምጧል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.