"ወደ ህክምና ትምህርት ቤት መሄድ ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል" — ኤለን ማስክ
በቢሊየነሩ ኤለን ማስክ እና በፒተር ዲያማንዲስ መካከል በተካሄደው "Moonshots" በተሰኘው የፖድካስት ውይይት ላይ ማስክ በህክምናው ዘርፍ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል። እንደ ማስክ ገለጻ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ ሮቦቶች በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ውስጥ በሰርጀሪ ወይም በቀዶ ጥገና ስራዎች ላይ ከሰዎች የተሻለ ብቃት ሊያሳዩ ስለሚችሉ፣ ወደ ህክምና ትምህርት ቤት መሄድ "ትርጉም አልባ" ሊሆን ይችላል።
"ጥሩ ሐኪም ለመሆን በጣም ረጅም ጊዜ ይወስዳል፤ ሐኪሞች ደግሞ የተወሰነ ጊዜ ነው ያላቸው፣ ስህተትም ይሰራሉ። ስንት ምርጥ የቀዶ ጥገና ሐኪሞችስ አሉ? ብዙ አይደሉም" ሲሉ ማስክ የዘርፉን ተግዳሮቶች ጠቅሰዋል። አቅራቢው ዲያማንዲስ "ታዲያ ወደ ህክምና ትምህርት ቤት አንሂድ?" ሲል ላቀረበለት ጥያቄ ማስክ "አዎ፣ ትርጉም የለውም" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ለዚህም እንደ ማሳያ የጠቀሱት የራሳቸውን ኩባንያ 'ኒውራሊንክ' የቀዶ ጥገና ሮቦት ሲሆን፣ ማሽኖች እጅግ ጥንቃቄ የሚሹ የህክምና ሂደቶችን በከፍተኛ ትክክለኛነት ማከናወን መጀመራቸውን በማሳያነት አቅርበዋል። ይህ የኤለን ማስክ አስተያየት ሮቦቶች ከሐኪም ረዳትነት ተሻግረው ራሳቸውን ችለው ቀዶ ጥገና ወደሚያከናውኑበት ደረጃ ስለመሸጋገራቸው ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይሁን እንጂ የኤለን ማስክ ንግግር በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሰው ልጅ የህክምና ውሳኔ ሰጪነት መካከል ስላለው ፍጥጫ አዲስ ክርክር ቀስቅሷል። አንዳንዶች የቴክኖሎጂውን እድገት ሲደግፉ፣ ሌሎች ደግሞ በህክምናው ዘርፍ የሰው ልጅ ጥንቃቄና የሞራል ውሳኔ በማሽኖች ሊተካ እንደማይችል እየገለጹ ይገኛሉ።
seledadotio

9 months ago