በጋምቤላ ከተማ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ የታገደ ሲሆን የንግድ ተቋማት የሥራ ሰዓትም ተገደበ
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በከተማው ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ከመንግስት የጸጥታ አካላት ጋር በዝርዝር ከተወያየ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል። ከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን አዳዲስ መመሪያዎች ከዛሬ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ወስኗል።
በአስተዳደሩ ውሳኔ መሠረት ማንኛውም የመንግሥትም ሆነ የግል ሞተር ሳይክል ከነገ ጀምሮ ለላልተወሰነ ጊዜ በከተማዋ ውስጥ ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ ሆኗል። የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተም በከተማው የሚገኙ ባጃጆች ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የተወሰነ ሲሆን፣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በከተማው የሚገኙ ሆቴሎችና ግሮሰሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ብቻ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል። እነዚህን የወጡ መመሪያዎች ጥሶ በሚገኝ በማንኛውም ግለሰብ ላይ አስተዳደሩ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በማሳሰብ ነዋሪዎችና የንግድ ማህበረሰቡ ውሳኔውን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርቧል።
seledadotio

9 months ago