Logo
Getu Temesgen
የአርሰናሉ ተጫዋች በሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያን ምድር ይረግጣል
#ethiopia | የቀድሞ የአርሰናልና የማን.ሲቲ እንደዚሁም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው ባካሪ ሳኛ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው።

የቀድሞው የአርሰናል እና የማንችስተር ሲቲ የመስመር ተከላካይ ባካሪ ሳኛ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ልምዱን እንደሚያካፍል ነው የተነገረው።

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአለም አቀፍ ተቋሞች ጋር ግንኙነት እንዲፈጠር እየሰራ የሚገኘው ዮሀንስ ዘውዱ ወይንም በተለምዶ ጆኒ ቬጋስ አማካኝነት ነው ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ተብሏል።

ኢትዮጵያዊው የእግርኳስ ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣም ይፋ አድርጓል።

ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣም ከአርሰናል ደጋፊዎች ጋር ይገናኛል የአርሰናል ኦርጅናል ማለያም ያበረክታል ብሏል።

ባካሪ ሳኛ በኢትዮጵያ የሚያደርገው ቆይታ ለምን ያህል ቀን እንደሆነ አልተገለጸም።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.