በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42 የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠ
የፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶማሊያ ባካሄዱት መጠነ ሰፊ የካልሚስካድ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር የዋሉ የውጭ ሀገር የISIS ታጋዮችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል በዚህ መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ታጋዮች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ማለትም ሀያ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታውቋል
ይህም ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኑ ISIS በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ የቅጥር እና የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው
በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መሆናቸው ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል። ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ የየመን፣ የቱርክ፣ የሞሮኮ እና የታንዛኒያ ዜጎች በቡድኑ ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል።
ይህ አሳሳቢ መረጃ እንደሚያመለክተው አክራሪ ኃይሎች በሀገሪቱ ውስጥ በስውር መረባቸውን በመዘርጋት ወጣቶችን ለሽብር ተግባር እያሰለጠኑ ወደ ጎረቤት ሀገራት እያሰማሩ ይገኛሉ
በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት በሃይማኖት አክራሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል ይህንን ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ ያለን አደገኛ እንቅስቃሴ ከወዲሁ ሊታገለው ይገባል
የሀገሪቱን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅም በስውር የሚንቀሳቀሱ የሽብር መረቦችን የመበጣጠስ ስራ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
በመሆኑም መንግስት ከጎረቤት ሀገራት የደህንነት ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ያለውን ጥብቅ ክትትል በማስቀጠል ይህንን ስር እየሰደደ የመጣውን የአክራሪነት ስጋት ሳይባባስ ሊያስቆመው እንደሚገባ ተመልክቷል
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ይፋዊ ምላሽ እናቀርባለን

9 months ago