Logo
FIDEL POST NEWS
በአዲስ አበባ እምብርት የሚገኘው "አራዳ ሞል" 48 በመቶ ይዞታውን ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች መመደቡን አስታወቀ
​
ሞሉ ከአሜሪካው ግዙፍ የቤት ዕቃዎች አምራች "አሽሊ ፈርኒቸር" ተወካይ (ዩስራ ሆም ፈርኒቸር) ጋር ለየት ያለ ሾው ሩም ለመክፈት ተፈራርሟል። አሽሊ ፈርኒቸር በዓለም ዙሪያ ከ1,000 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ግዙፍ ተቋም ነው።

​🏢 የቦታ ክፍፍል፦ ከህንፃው ጠቅላላ ይዞታ 48% ለውጭ ኩባንያዎች የተመደበ ሲሆን፣ ቀሪው 52% ደግሞ ለሀገር ውስጥ ድርጅቶች በኪራይ የሚተላለፍ ይሆናል።

​👷‍♂️ የሥራ ዕድል፦ በ16,500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት እስካሁን ለ1,200 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

​✨ ምን ምን ይይዛል?

👉​ዓለም አቀፍ የፋሽን ብራንዶች
👉​ሲኒማ፣ ጅምናዚየም እና የልጆች መጫወቻ
👉​ከቀረጥ ነፃ (Duty Free) መሸጫዎች
👉​ባንኮች እና የካፌ አገልግሎቶች

​ዘመናዊ የምህንድስና ጥበብ የታየበት ይህ ሞል፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ባለሙያዎች ጥምረት የተቀረጸ ልዩ ዲዛይን እንዳለው ተገልጿል።
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.